ይፋ ያልሆነ ፡ ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ሲወሰንበት ለሀዋሳ ከተማ ፎርፌ ተሰጥቷል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው አርብ በአዲስ አበባ ስታድየም ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ የተከሰተው የስታድየም ረብሻን ተከትሎ በኢትዮጵያ ቡና ላይ ቅጣት ጥሏል፡፡

በቅታት ውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያ ቡና ከ ሃዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ለሀዋሳ ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ንፁህ ግብ) እንዲሰጥ ከውሳኔ የደረሰ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ የሚያካሂዳቸው 2 ጨዋታዎችን ማለትም ከወላይታ ድቻ እና ከድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡ በረብሻው የወደሙ ንብረቶች ተተምነው ከፍያ እንዲፈፀምም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቅጣት ውሳኔውን ይፋ ሲያደርግ ሙሉ ዘገባ ይዘን የምንመለስ ይሆናል፡፡

PicsArt_1465595306923

4 thoughts on “ይፋ ያልሆነ ፡ ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ሲወሰንበት ለሀዋሳ ከተማ ፎርፌ ተሰጥቷል

 • June 15, 2016 at 7:48 pm
  Permalink

  ይገርማል!!! የፌዴርሽኑ ባለስልጣናት ለምን 35ሺ ብቻ ዳሽንን ቀጣቹ ተብለው ሲጠየቁ መልሳቸው ከፍተኛው ቅጣት መመሪያው የሚያዘው ይሄ ነው ብለው ነበር ዛሬ ግን የቡና ደጋፊ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ሲጋጭ መመሪያው ተሽሮ 50ሺ ብር ሆነ ይሄ መመሪያ ሲጣስ ምን ማለት ይኖርብን ይሆን?

 • June 14, 2016 at 5:21 pm
  Permalink

  woldya kenema laym temesasay kitat metal alebet lik ende Ethiopia buna degafiwech wede meda eyewereweru ye amhara wuhe sira techawachochin simetu neber chewatawum 2nd half bezih mknyat tekurtual temesasay kitat litalbet yigebal

 • June 14, 2016 at 3:15 pm
  Permalink

  በጣም የሚገርመው ነገር ዳሸን ቢራ ላይ ያለምንም ማስረጃ የተወሰነው ኢ ፍታዊ የሆነ ፍርድ በጣም ይገርማል ይህ ሁሉ ጥፋት የቡና ደጋፊ አጥፍቶ የተላለፈው ውሳኔ በተቃራኒው መሆኑ ይገርማል ለአዲስ አበባ ክለቦች አቀንቃኝ የሆኑ የ ሬድዩ ጣቢያዎች ለ እግር ኳሱ እድግት እንቅፋት ብቻ ሳይሆኑ መሸሸጊይ ጭምር መሆናቸው ሌላው አስገራሚው ነገር ነው

 • June 14, 2016 at 2:33 pm
  Permalink

  1ጓደኛዬ “አዲስ አበባ ስቴዲየም ገብቼ እግር ኳስ ስመልከት ልክ በ*** ሰፈር ውስጥ በምሽት ስሄድ የሚሰማኝ አይነት ስጋት ይሰማኛል ጀምሯል” ሲለኝ በጣም ነበር የገረመኝ… ከምንም በላይ “እኛ ስንሆን ብቻ ነው ህጉን የሚጠቀሙት” የምትለዋ ወሬ ለረባሾቹ ጥሩ ምክንያት ሆናቸዋለች:: ለጨዋ እና እውነተኛዎቹ የቡና ደጋፊዎች ከልብ አዝናለሁ! በተወሰኑ ጋጠወጧች ምክንያት “ድሮስ ከቡና ደጋፊ” አብረው ሲወቀሱ መስማት ያሳዝናል:: እምንወደውን እግር ኳስ የተሻለ ለማድረግ ሁላችንም በአነድ ላይ መቆም አለብን!!!

Leave a Reply

error: