አዲሱ የወልድያ ሼክ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ ስታድየም ገፅታ

በወልድያ ከተማ የተገነባው የሼክ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ ስታድየም ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡ ስታድየሙን የጎበኘው ባልደረባችን መሀመድ አህመድ ስለስታድየሙ ያሰባሰበውን መረጃ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

መቻሬ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የተገነባው ይህ ስታድየም የግንባታ ሂደቱ 4 አመት ያህል የፈጀ ሲሆን ከግማሽ ቢልዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ይታመናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ወንበር እና ጣርያ የተገጠመለት ስታድየሙ 25ሺህ ሰዎችን በወንበር የማስተናገድ አቅም አለው፡፡

4 የመልበሻ ከፍሎች እና 2 የማሟሟቂያ ሜዳዎቸ ያሉት ስታድየሙ ከዋናው የእግርኳስ እና አትሌቲክስ ሜዳ በተጨማሪ በውጭኛው ስታድየም ክፍል የዋና ገንዳ ፣ የቅርጫት ኳስ ፣ መረብ ኳስ ፣ እጅ ኳስ እና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎች እንዲሁም ለ34 ሰዎች የሚሆን የእንግዳ ማረፍያ አካቷል፡፡

ልክ እንደ አዲስ አበባ ስታድየም ሁሉ በዙርያው ከመቶ በላይ የንግድ ሱቆች የተዘጋጀለት አዲሱ የወልድያ ስታድየም የሄሊኮፍተር ማረፍያ ፣ በቂ የመኪና ማቆምያ እና ውብ አረንጓዴ ቦታዎች አሟልቷል፡፡

ወደ ስታድየሙ ውስጠኛ ክፍል ስናመራ ሁለት ግዙፍ ስክሪኖች እንደሚገጠም የታወቀ ሲሆን 2 የቪአይፒ ቦታዎች ተዘጋጅተውለታል፡፡ አንደኛው በመስታውት የተከለለና ለደህንነት አስተማማኝ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መስታውት የሌለው የቪአይፒ መቀመጫዎች ስፍራ ነው፡፡ በዘመናዊ መንገድ የተሰራ የጋዜጠኞች ክፍል ሲኖረው በአንድ ጊዜ በርካታ ሚድያዎች ጨዋታ በቀጥታ እንዲያስተላልፉ በማሰብ የድምፅ መደበላለቅ እንዳይፈጠር ድምፅ የማያሳልፉ ክፍሎችም ተዘጋጅተውለታል፡፡ በትሪቡን በኩል የኤሌክትሮኒክስ መፈተሻ እንደተገጠመለትም ታውቋል፡፡

ይህ ሙሉ ለሙሉ ወንበር የተገጠመለት ዘመናዊ ስታድየም በመጪው ጥቅምት ወር 2009 እንደሚመረቅ የታወቀ ሲሆን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማለፍ እጅግ ጥቂት እርምጃ ብቻ የቀረው ወልድያ ስፖርት ክለብ የቀጣይ የውድድር ዘመኑን ሙሉ መቀመጫው በክለቡ የማልያ ቀለም ባሸበረቀው ዘመናዊ ስታድየም የሚጫወት ይሆናል፡፡

ከስታድየሙ የውስጥ ገፅታዎች የተወሰኑ ምስሎችን እነሆ ብለናል፡-

PicsArt_1469960781074 PicsArt_1469960747506 PicsArt_1469960689070 PicsArt_1469960637185 PicsArt_1469960585268 PicsArt_1469960548057 PicsArt_1469960467250 PicsArt_1469960399133

ሙሐመድ አህመድ

ይህን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ሙሐመድ አህመድ ነኝ፡፡

4 thoughts on “አዲሱ የወልድያ ሼክ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ ስታድየም ገፅታ

 • August 1, 2016 at 6:36 am
  Permalink

  እናመሰግናለን ሶከር ኢትዪጵያዎች ምን ጊዜም ወልድያ አንድ ደረጃ ከፍ እንላለን

 • July 31, 2016 at 10:37 pm
  Permalink

  Wow betam arif nw lelochim yehagerachin cleboch yerasachew yehone stadium biseru tiru nw

 • July 31, 2016 at 10:37 pm
  Permalink

  አዲስ አበባ ቢሄን እንዴት አሪፍ ነበር! አልታደልንም

Leave a Reply

error: