ኮፓ ኮካኮላ ፡ በወንዶች አማራ እና ደቡብ ለፍጻሜ አልፈዋል

የኮፓ ኮካኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር የወንዶች የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ወደ ፍጻሜው የተሸጋገሩት ቡድኖች ታውቀዋል፡፡

03:00 ላይ አማራ ኦሮምያን 2-0 በመርታት ወደ ፍጻሜው አልፏል፡፡ በ46ኛው ደቂቃ ሞላዬ አብላ የመታውን ቅጣት ምት ለሚ ተርፋሳ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥር ሱራፌል ሰለሞን በ65ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን አክሏል፡፡ በውድድሩ የተደራጀ እንቅስቃሴ በማሳየት አድናቆት ያገኙች ኦሮምያዎች በዛሬው ጨዋታ ተዳክመው ታይተዋል፡፡

PicsArt_1472821188258

05:00 ላይ ደቡብ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛው ክፍለ ጊዜ 2-2 ተጠናቆ በመለያ ምቶች ደቡብ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ደቡብ በ11ኛው ደቂቃ እስጢፋኖስ ዘውዴ ባስቆጠረው ግብ ቀዳሚ ቢሆኑም በቅጽበት የደቡብን በር የፈተሹት ቤኒሻንጉሎች ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት በአብድ ህዝቅኤል አማካኝነት ወደ ግብነት ቀይረው አቻ ሆነዋል፡፡ መልካሙ አሰፋ በ39ኛው ደቂቃ ደቡብን በድጋሚ መሪ ሲያደርግ አብዱሃሲቅ ሃሺም በ51ኛው ደቂቃ ቤኒሻንጉልን አቻ አድርጓል፡፡

መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2-2 መጠናቀቁን ተከትሎ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች ደቡብ 3-0 አሸንፏል፡፡ ግብ ጠባቂው ዳንኤል ሰይፉም ከተመቱት የመለያ ምቶች መካከል ሁለቱን በማዳን ለድሉ ትልቁን ድርሻ ወስዷል፡፡ ደቡብ ክልልም በሁለቱም ጾታዎች ለፍጻሜ መድረስ ችሏል፡፡

ልክ የዛሬ ሳምንት አርብ በሴቶች ውድድር የተጀመረው የ2008 የኮፓ ኮካኮላ የማጠቃለያ ውድድር እሁድ ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ ነገ በሴቶች የ3ኛ ደረጃ ጨዋታ 09:00 ላይ ቤኒሻንጉል ከ አዲስ አበባ ሲጫወቱ በወንዶች 3ኛ ደረጀ ጨዋታ ቤኒሻንጉል ከ ኦሮምያ እሁድ ጠዋት 1:00 ላይ በለምለም ተስፋ ት/ቤት ይጫወታሉ፡፡

እሁድ 02:00 ቢሾፍቱ ስታድየም ላይ ደቡብ ከ ኦሮሚያ ለሴቶች ዋንጫ ሲፋለሙ 04:00 ላይ ደቡብ ከ አማራ ለወንዶች ዋንጫ ይጫወታሉ፡፡ ከጨዋታዎቹ በኋላም የዋንጫ ፣ የሽልማት እና የመዝጊያ ስነስርአት ይካሄዳል፡፡

አብርሃም ገብረማርያም
Follow Me

አብርሃም ገብረማርያም

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ አብርሃም ገብረማርያም ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
አብርሃም ገብረማርያም
Follow Me

አብርሃም ገብረማርያም

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ አብርሃም ገብረማርያም ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

One thought on “ኮፓ ኮካኮላ ፡ በወንዶች አማራ እና ደቡብ ለፍጻሜ አልፈዋል

  • September 2, 2016 at 6:46 pm
    Permalink

    SNNPR is home land of Ethiopian football.

    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *