የሙሉጌታ ምህረት የሽኝት ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ

  ዜና | 18-01-2009 

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከእግርኳስ ተጫዋችነት ለተገለለው ሙሉጌታ ምህረት የክብር መሸኛ የተዘጋጁ ጨዋታዎች እሁድ እንደሚካሄዱ የጨዋታዎቹ አዘጋጅ አስታውቋል፡፡

በሃዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም በሚከናወነው ፕሮግራም ሁለት ጨዋታዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከናወኑ ታውቋል፡፡

08፡00 ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሲዳማ ቡና ሲጫወቱ 10፡00 ሙሉጌታ ምህረት ተጫውቶ ያለፈባቸው ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ በእለቱ ሙሉጌታ ምህረት በሁለተኛው ጨዋታ (ሀዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ) ላይ ለሁለቱም ክለቦች በየተራ እንደሚጫወትም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በእለቱ በርካታ አዝናኝ ፕሮግራሞች የተዘጋጁ ሲሆን የቀድሞ ተጨዋቾች ግጥሚያም ሊኖር እንደሚችል እና ከአዲስ አበባ እና ከሀዋሳ የተወጣጡ የሙሉጌታ ምህረት ጓደኞች ግጥሚያም ይኖራል ተብሏል፡፡

አዘጋጆቹ መስከረም 22 የስፖርት ቤተሰቡ በሃዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በመገኘት ለሙሉጌታ ምህረት ያላቸውን ክብር እንዲያሳዩ እና ባሉት የመዝናኛ ፕሮግራሞች እንዲዝናኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

3 thoughts on “የሙሉጌታ ምህረት የሽኝት ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ

  • September 29, 2016 at 12:05 pm
    Permalink

    ለሙሊዬ ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም ሙሊዬ በአሰልጣኝነትም ብቃቱን እያሳዬን ነዉ!!! ሙሊዬ እንወድሀለን

  • September 28, 2016 at 8:50 pm
    Permalink

    Aree ayikerm………………………….. leamele shegaw Muluye yigebawal endewm yihe siyansew nw ………………………….. Ehud ebgenagn

Leave a Reply

error: