ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንሰ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT ቅዱስ ጊዮርጊስ   0-1  ሰንዳውንስ 

85′ አንቶኒ ላፎር


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በሰንዳውንስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ የማሸነፍ እድልም አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሰንዳውንስ
90′
ግቡን ያስቆጠረው ላፎር ወጥቶ ሀቺ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሰንዳውንስ
87′
ታኦ ወጥቶ ንቴቴ ገብቷል

ጎልልል!!
85′ አንቶኒ ላፎር ከግራ መስመር የተሻገረለትን ኳስ ተጠቀሞ ሰንዳውንስን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
81′
ፍሬዘር ካሳ ወጥቶ ብሩኖ ኮኔ ገብቷል

80′ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ቢደርሱም በማጥቃት ወረዳው ላይ ያላቸው ስኬት ዝቅተኛ ነው፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
76′
በኃይሉ አሰፋ ወጥቶ ያስር ሙገርዋ ገብቷል

የተጫዋች ለውጥ – ሰንዳውንስ
68′
ያኒክ ወጥቶ ታፌሎ ገብቷል፡፡

64′ ሮበርት ኦዶንካራ ከርቀት የተሞከረውን ኳስ ወደ ውጪ አውጥቶታል፡፡ ሰንዳውንሶች ከመጀመርያው አጋማሽ በተሻለ ወደ ጊዮርጊስ የግብ ክልል እየተጠጉ ይገኛሉ፡፡ 

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱር ጊዮርጊስ
63′
ፕሪንስ ወጥቶ ወጥቶ አዳነ ግርማ ገብቷል

56′ በኃይሉ አሰፋ በፍጹም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ መልካም አጋጣሚ ቢያገኝም የመታው ኳስ ጥንካሬ የሌለው በመሆኑ ኦንያንጎ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

50′ የሁለተኛው አጋማሽ የመጀመርያ 5 ደቂቃዎች የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ አስተናግዷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛውአጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በሳላዲን ሰኢድ አማካኝነት ተጀመረ፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ሳተ!
45′ የፍጹም ቅጣት ምቱን ሳላዲን መትቶ ኦንያንጎ መልሶበታል፡፡

ፍቅም!
45′ ፕሪንስ ከሳጥን ውጪ የሞከረውን ኳስ ተከላካዮች ሲደረቡበት በቅርብ የነበረው በኃይሉ አግኝቶ ሲመታ የሳንዳውንስ ተከላካይ ኳሷን በእጁ በመንካቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቷል ።

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

43′ ኒኪማ ከፕሪንስ የተቀበለውን ኳስ በቀኝ እግሩ መሬት ለመሬት ሞክሮ በግቡ ቋሚ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

41′ ኒኪማ ከሳላዲን ሰኢድ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

30′ ጨዋታው መሀል ሜዳ ላይ ያመዘነ ነው ። ሳዳውንሶች ጥንቃቄ የተሞላበት አጨዋወትን የመረጡ ይመስላሉ ። ጊዮርጊሶች ግብ ማስቆጠሪያ ቀዳዳዎችን ለማግኘት እየሞከሩ ይገኛሉ ሆኖም የሜዳው ሁኔታ ጨዋታውን ከባድ አድርጎታል፡፡ 

15′ ላንገርማን ከሳጥን ውጪ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።

12′ ላፉር የሞከረው ኳስ ወደላይ ተነስቶ ወጥቷል ።

11′  ሳንዳውንሶች ወደጨዋታው መንፈስ እየተመለሱ ይገኛሉ ።

9′ ሳላዲን ከረጅም ርቀት የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።

7′ በሀይሉ ያሻማውን ኳስ ኦን6ኣንጎ ሲያድነው አግኝቶ ፕሪንስ ከቅርብ ርቀት ቢሞክርም በሚያስቆጭ መልኩ ስቶታል ።

6′ ኒኪማ ከርቀት የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።

5′ በሀይሉ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሞዳይስ አወጣለው ብሎ የጨረፈው ኳስ አንግል መታ ወታለች ።

ተጀመረ!
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

ሮበርት ኦዶንካራ

ፍሬዘር ካሳ – ደጉ ደበበ – አስቻለው ታመነ – አበባው ቡጣቆ

ምንተስኖት አዳነ – ናትናኤል ዘለቀ

ፕሪንስ ሰቬርኒሆ – አብዱልከሪም ኒኪማ – በኃይሉ አሰፋ

ሳላዲን ሰዒድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *