አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በወላይታ ድቻ ውላቸውን አደሱ

የኢትዮጵያ ዋንጫ ቻምፒዮኑ ወላይታ ድቻ የአሰልጣኙ መሳይ ተፈሪን ውል ለተጨማሪ ሁለት የውድድር ዘመናት ለማደስ ከስምምነት ደርሷል፡፡ አሰልጣኙ ከድቻ ጋር የተስማሙበትን የክፍያ መጠን ክለቡ ከመግለጽ ቢቆጠብም ከዚህ ቀደም ከሚያገኙት የተሻሻለ ክፍያ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

ከስምምነቱ መጠናቀቅ በኋላ ለሶከር ኢትዮዽያ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በቀጣይ በፕሪምየር ሊጉ እና ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ማድረግ እቅዳቸው እንደሆነ ተናግረው ለዚህ እንዲረዳቸውም ቀድሞ ከነበረው የተጫዋች ግዢ ፖሊስያቸው የተወሰነ ለውጥ እንደሚኖር ተናግረዋል።

ወላይታ ድቻ በ2001 ሲመሰረት አሰልጣኝ ተደርገው የተሾሙት የቀድሞው የአርባምንጭ ጨጨ እና ኢትዮጵያ ቡና ኮከብ መሳይ ተፈሪ ላለፉት 8 አመታት በወላይታ ድቻ የቆዩ ሲሆን ወላይታ ድቻ ከሌሎች ክለቦች በተለየ የሚመድበውን ዝቅተኛ በጀት በመጠቀም ተፎካካሪ ቡድን በመገንባት መልካም ስም አትርፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *