አፍሪካ፡ ጅቡቲ የኢትዮጵያን ሽንፈት ተከትሎ ብሔራዊ ቡድኗን በተነች

የጅቡቲ እግርኳስ ፌድሬሽን የሃገሪቱን ብሄራዊ ቡድን መበተኗን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡ ጅቡቲ በአፍሪካ ዋንጫ፣ የአለም ዋንጫ፣ ቻን ማጣሪያዎች እንዲሁም የሴካፋ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ የምታስመዘግበው ውጤት መጥፎ መሆኑ የሃገሪቱ ፌድሬሽን ወደ እዚህ ውሳኔ እንዲደርስ እንዳደረገው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጅቡቲ በኢትዮጵያ ኬንያ በ2018 ለምታስተናግደው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና (ቻን) 5-1 ከተረታች በኃላ የመልሱን ጨዋታ ሀዋሳ ላይ እንዳማታደርግ በሳምንቱ መጀመሪያ ያሳወቀች ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ከካፍ የገንዘብ ቅጣት በደንቡ መሰረት እንደሚኖር ተነግሯል፡፡ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኘው ጅቡቲ ደቡብ ሱዳን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በሜዳዋ ካሸነፈችበት የ2-0 ውጤት ውጪ በሌሎች ጨዋታዎች በሰፊ ግብ ልዩነት ስትሸነፍ ነበር፡፡ በዚህም ብሄራዊ ቡድኗን ከአሰልጣኝ ቡድን አባላቱ ጭምር በትናለች፡፡ ፊቷንም ታዳጊዎች ወደ ማብቃት ማዞሯ ተነግሯል፡፡

የጅቡቲ እግርኳስ ፌድሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር ኦማር አሊ መሃመድ ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት ወደ ወጣቶች እግርኳስ ትኩረት እንዲሚያደርጉ ነው፡፡ “ቡድኑ ውጤት ስለሌለው ትኩረታችንን ለወጣቶች እግርኳስ ሰጥተናል፡፡ ምንአልባትም ከ15፣ 17 እና 20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ እንሳተፋለን፡፡”

ኦማር አሊ ሲቀጥሉ በገንዘብ ችግር ምክንያት ቡድኑን ለመበተን እንዳልተገደዱ አስረድተዋል፡፡ “የገንዘብ ችግር የለብንም፡፡ ይህ የፌድሬሽኑ አዲስ ፖሊሲ ነው፡፡”
እንደፌድሬሽኑ አቋም በተደጋጋሚ ቡድኑ ከሚደርስበት ከባድ ሽንፈት ምክንያት የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *