ምንያህል ተሾመ ወደ ወልድያ አመራ

ወልዲያ ስፖርት ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ምንያህል ተሾመን ማስፈረሙን በኦፊሴላዊው የፌስቡክ ገፁ ይፋ አደርጓል፡፡ ከፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የአራት ዓመት ቆይታ በኃላ ውሉን በማጠናቀቁ ወደ ወልዲያ ማምራቱ ታውቋል፡፡

ምንያህል በዝውውር መስኮቱ ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ጋር ስሙ በስፋት ተያይዞ የተነሳ ቢሆንም ወልዲያ ቀጣይ ማረፊያው ሆኗል፡፡ ምንያህል በዘንድሮው የውድድር ዘመን በጉዳት ምክንያት ለፈረሰኞቹ እምብዛም አገልግሎት አልሰጠም፡፡ 

አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ ወደ ወልዲያ ከመጡ በኃላ ክለቡ በዝውውር ገበያው ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል፡፡ ምንያህል የወልዲያ 10ኛ ፈራሚ ሲሆን ክለቡ እስካሁን ያስፈረማቸው አመዛኞቹ ተጫዋቾች የመከላካል ባህሪ ያላቸው መሆናቸው ተከትሎ የምንያህል መምጣት እንደድክመት የሚታየውን የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያሻሽለዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንያህል ለስድስት ጉዜያት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ከኢትዮጵያ ቡና (2003)፣ ደደቢት (2005) እና ቅዱስ ጊዮርጊስ (2006፣2007፣2008፣2009) ጋር የሊጉ ዋንጫ ክብርን ማሳካት ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *