ወላይታ ድቻ ጃኮ አረፋት እና አምረላህ ደልታታን አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ወላይታ ድቻ የሁለት ተጫዋቾችን ፊርማ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ጃኮ አራፋት እና አምራላ ደልታታም ለክለቡ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በመጀመሪው አመት ነጥረው ከወጡ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው እና ለሀዋሳ ከተማ 12 የሊግ ግቦች በማስቆጠር ድንቅ አመት ያሳለፈው የቀድሞው የአንዚ ማካቻካላ እና ሲኤፍ ሞናና አጥቂ ስሙ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክለቦች እና የእስራኤል ፕሪምየር ሊግ ክለቡ የሆነው ሀፖኤል አክሬ ጋር ቢያያዝም ለእረፍት ካመራበት ሀገሩ በመምጣት በቃል ደረጃ ተስማምቶበት የነበረው ወላይታ ድቻን በአንድ አመት ውል መቀላቀሉ ታውቋል፡፡

ሌላኛው የወላይታ ድቻ ፈራሚ የሆነው አምረላ ደልታታ ነው፡፡ በሀዲያ ሆሳዕና ጋር ሁለት የውድድር ዘመናትን ማሳለፍ የቻለው የቀኝ መስመር አማካዩ ሀዲያ ሆሳዕና ምንም እንኳን በዘንድሮው አመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባይቀላቀልም መልካም የውድድር አመት ማሳለፍ ችሏል፡፡

ወላይታ ድቻ በዝውውር መስኮቱ ሁለቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 9 ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *