ማናዬ ፋንቱ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቀለ

በኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች የሙከራ ጊዜ የተሰጠው ማናዬ ፋንቱ በቆይታው አመርቂ እንቅስቃሴ በማድረጉ ለክለቡ ፈርሟል፡፡

ፈጣኑ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ከ6 አመት በፊት ደቡብ ፖሊስን ለቆ ወደ መከላከያ በማምራት ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተመርጦ በ2014 የቻን ጨዋታዎች ላይም መሰለፍ ችሎ ነበር፡፡ በ2007 ክረምት ወደ ኤሌክትሪክ ካመራ በኋላ ግን በተለይ ዘንድሮ በጉዳት ለክለቡ ግልጋሎት ሳይሰጥ የውል ዘመኑ ተጠናቋል፡፡

ማናዬ ወደ ቀድሞ የአካል ብቃት ደረጃው ለመመለስ በግሉ ጠንካራ ልምምዶችን ሲሰራ እንደቆየ የተገለጸ ሲሆን በሙከራ ቆይታው ድራጋን ፖፓዲችን በማሳመኑ የሁለት አመት ኮንትራት ፈርሞ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *