ፕሪምየር ሊጉ የሚጀመርበት ቀን ለ3ኛ ጊዜ ተራዘመ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሪምየር ሊግ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ እና የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመሩበት ቀናት ላይ መሸጋሸግ አድርጓል፡፡

በተራዘመው መርሃ ግብር መሰረት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ይጀመራል ከተባለበት ጥቅምት 18 በአንድ ሳምንት ተገፍቶ ወደ ጥቅምት 25 እና 26 ተሸጋግሯል፡፡ ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ መገፋት የክለቦች ጥያቄ እና የአአ ከተማ ዋንጫ ዘግይቶ መጠናቀቅን በምክንያትነት አስቀምጧል፡፡ የዘንድሮው የውድድር አመት ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ሲለወጥ ይህ ለ3ኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ጥቅምት 4 ይጀመራል ቢባልም ወደ ጥቅምት 11 እና ጥቅምት 18 መገፋቱ ይታወሳል፡፡

ከሊጉ መጀመር በፊት የሚደረገው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ እሁድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 እንዲደረግ ተወስኗል፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ መካከል የሚደረገው ይህ መርሃ ግብር በቅድሚያ በደርሶ መልስ መልክ መስከረም 25 እና 28 እንዲካሄድ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም በዝናብ እና የሲቲ ካፕ ምክንያ ወደ ጥቅምት 4 ተሸጋግሮ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ጥቅምት 19 አዲስ አበባ ስታድየም ላይ እንዲደረግ ተወስኗል፡፡

ሌላው የመርሃ ግብር ለውጥ የተደረገበት የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ነው፡፡ ጥቅምት 17 ሊጀመር የታሰበው ውድድር ወደ ጥቅምት 25 አሁን ደግሞ ወደ ወደ ህዳር 2 ተሸጋግሯል፡፡

[table id=383 /]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *