​የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች ዝውውር ሲጠቃለል…

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የዝውውር መስኮት በትላንትናው እለት መዘጋቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ሐምሌ 5 ቀን 2009 በይፋ የተጀመረው የዝውውር እንቅስቃሴ በርካታ ዝውውሮች ተከናውነውበታል፡፡

ምን ያህል ተዘዋወሩ?

በዝውውሩ በ120 ቀናት የዝውውር እንቅስቃሴ 156 ተጫዋቾች ለአዲስ ክለባቸው ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ከነዚህ መካከል ደግሞ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ሌሎች ክለቦች በውሰት ያመሩ ናቸው፡፡ በሊጉ በአረንጓዴ መታወቂያ ከተመዘገቡ 400 ተጫዋቾች መካከልም ሌሎች ክለቦችን ለቀው አዲስ ክለብ የተቀላቀሉት 40 በመቶ የሚሆኑት ናቸው፡፡ ይህም ማለት በአንድ ክለብ ውስጥ ከሚገኙ 25 ተጫዋቾች መካከል በአማካይ ከ9 – 10 አዳዲስ ተጫዋቾች ይገኛሉ፡፡   

ከየት መጡ? 

ከ156 አዳዲስ ፈራሚዎች መካከል ከላይ በምስሉ ላይ እንደተመለከተው በፕሪምየር ሊጉ አምና የተጫወቱ 105 ተጫዋቾች ዘንድሮም ወደ ሌላ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ተዘዋውረው የምንመለከታቸው ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ከፈረሙት ተጫዋቾች ዘንድሮ 35 ተጫዋቾችን (22 በመቶ) ለሊጉ አዲስ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ 

የውጪ ዜጎች 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2010 የውድድር ዘመን 54 የውጪ ዜጎች የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ከነዚህ መካከል 24 ተጫዋቾች ለሊጉ አዲስ ሲሆኑ ሁለት ተጫዋቾች (ፊሊፕ ዳውዝ እና ሴሴንቶንጎ) ከዚሀ ቀደም በኢትዮጵያ ሊግ የተጫወቱና ዘንድሮ ወደ ሊጉ የተመለሱ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 31 ተጫዋቾች ደግሞ ከአምና ወይም ከዛ በፊት ጀምሮ በሊጉ እየተጫወቱ የሚገኙ ናቸው፡፡

በ15 ክለቦች ውስጥ ቢያንስ ሁለት የውጪ ዜጋ ተጫዋች የሚጫወት ሲሆን መከላከያ ብቻ በሊጉ አንድም የውጪ ዜጋ በስብስቡ ውስጥ የማይገኝ ክለብ ነው፡፡

ግብ ጠባቂዎች

የዘንድሮው የዝውውር መስኮት የክለቦቻችንን በኢትዮጵያውያን ግብ ጠባቂዎች ላይ ያላቸው እምነት ይበልጥ እየተሸረሸረ መሆኑን ያሳየ ሆኗል፡፡ አምና እና ከዛ ቀደም በሀገር ውሰጥ ግብ ጠባቂ ሲጠቀሙ የነበሩት ወላይታ ድቻ፣ መቀለ ከተማ ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከተማ የውጪ ግብ ጠባቂ ሲያስፈርሙ በአጠቃላይ ከ16 ክለቦች መካከል የውጪ ዜጋ ግብ ጠባቂ የሌላቸው ወልዋሎ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ድሬዳዋ ፣ አርባምንጭ እና መከላከያ ብቻ ናቸው፡፡

ማን ብዙ አስፈረመ?

ዘንድሮ ወደ ሊጉ ያደጉት ክለቦች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተጫዋች በማስፈረም ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ለክለቦች የፈረሙ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-

ጅማ አባ ጅፋር (16)

ዳዊት አሰፋ ፣ መላኩ ወልዴ ፣ ኄኖክ ኢሳይያስ ፣ ኄኖክ አዱኛ ፣ ቢንያም ሲራጅ ፣ አሸናፊ ሽብሩ ፣ ይሁን እንደሻው ፣ ዮናስ ገረመው ፣ ፍራኦል መንግስቱ ፣ ጌቱ ረፌራ ፣ አሚኑ ነስሩ ፣ እንዳለ ደባልቄ ፣ ሳምሶን ቆልቻ ፣ ዳንኤል አጄይ ፣ አዳማ ሲሶኮ ፣ ኦኪኪ አፎላቢ

መቐለ ከተማ (15)

ፊሊፕ ኢቮና ፣ አቼምፖንግ አሞስ ፣ ቢስማርክ አቦሜንግ ፣ ሚካኤል አካፉ ፣ ሚካኤል ደስታ ፣ ፍቃዱ ደነቀ ፣ አመለ ሚልኪያስ ፣ መድህኔ ታደሰ ፣ አንተነህ ገብረክርስቶስ ፣ ዳንኤል አድሀኖም ፣ ዮሴፍ ድንገቱ ፣ ሙሉጌታ ረጋሳ ፣ አለምነህ ግርማ ፣ ዱላ ሙላቱ ፣ ዮናስ ግርማይ 

ድሬዳዋ ከተማ (15)

ጀማል ጣሰው ፣ ሀምዲ ቶፊቅ ፣ አናጋው ባደገ ፣ ሙህዲን ሙሳ ፣ ወሊድ ቶፊቅ ፣ ዳኛቸው በቀለ ፣ አንተነህ ተስፋዬ ፣ አህመድ ረሺድ ፣ ወሰኑ ማዜ ፣ ያሬድ ዘውድነህ ፣ ዘካርያስ ፍቅሬ ፣ መሐመድ ጀማል ፣ ኩዋሜ አትራን ፣ ሰንደይ ሙቱኩ ፣ ሳውሬል ኦልሪሽ

ወልዋሎ (14)

በረከት ተሰማ ፣ ሮቤል ግርማ ፣ ተስፋዬ ዲባባ ፣ ዋለልኝ ገብሬ ፣ እንየው ካሳሁን ፣ ቢንያም አየለ ፣ ሙሉአለም ጥላሁን ፣ ብሩክ አየለ ፣ በለጠ ተስፋዬ ፣ ወግደረስ ታዬ ፣ እዮብ ወልደማርያም ፣ ዘውዱ መስፍን ፣ ፕሪንስ ሰቨሪንሆ ፣ አብዱራማን ፉሴይኒ

ኢትዮጵያ ቡና (13)

ወንድወሰን አሸናፊ ፣ ድንቅነህ ከበደ (በውሰት ለአአ ከተማ ተሰጥቷል) ፣ ቢንያም አድማሱ  (በውሰት ለአምበሪቾ ተሰጥቷል) ፣ አስራት ቱንጆ ፣ አብዱሰላም አማን ፣ ትዕግስቱ አበራ ፣ ሮቤል አስራት ፣ ቶማስ ስምረቱ ፣ አለማየሁ ሙለታ ፣ ንታምቢ ክሪዚስቶም ፣ ሳምሶን ጥላሁን ፣ ማናዬ ፋንቱ ፣ በረከት ይስሃቅ

ወልዲያ (12)

አማረ በቀለ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ ተስፋዬ አላባቸው ፣ ብሩክ ቃልቦሬ ፣ ፍፁም ገብረማርያም ፣ ምንያህል ተሾመ ፣ ደረጄ አለሙ ፣ ታደለ ምህረቴ ፣ ሰለሞን ገብረመድህን ፣ ተስፋሁን ሸጋው ፣ ብርሃኔ አንለይ ፣ ኤደም ኮድዞ

ኤሌክትሪክ (12)

ዮሀንስ በዛብህ ፣ ሞገስ ታደሰ ፣ ዘካርያስ ቱጂ ፣ ግርማ በቀለ ፣ ኄኖክ ካሳሁን ፣ ጥላሁን ወልዴ ፣ ቢንያም አሰፋ ፣ ጫላ ድሪባ ፣ ምንያህል ይመር ፣ ኃይሌ እሸቱ ፣ ካሉሻ አልሀሰን ፣ ዲዲዬ ለብሪ

ፋሲል ከተማ (11)

ቢንያም ሐብታሙ ፣ አይናለም ኃይለ ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ራምኬል ሎክ ፣ መሐመድ ናስር ፣ አቤል ውዱ ፣ ብሩክ ግርማ ፣ ያስር ሙገርዋ ፣ ፊሊፕ ዳውዚ ፣ ሮበርት ሴንቴንጎ ፣ ሚኬል ሳማኬ

ሲዳማ ቡና (10)

ወንድሜነህ አይናለም ፣ ምስጋናው ወልደዮሀንስ ፣ ባዬ ገዛኀኝ ፣ ሐብታሙ ገዛኸኝ ፣ ፈቱዲን ጀማል ፣ አምሀ በለጠ ፣ ሚካኤል አናን ፣ መሐመድ ቤን ኮናቴ ፣ ኬኔዲ አሺያ ፣ አብዱለጢፍ መሐመድ

ወላይታ ድቻ (9)

ተስፋ ኤልያስ ፣ ኃይማኖት ወርቁ ፣ እሸቱ መና ፣ አሳልፈው መኮንን ፣ እርቅይሁን ተስፋዬ ፣ አምረላ ደልታታ ፣ ማሳማ አሴልሞ ፣ ጃኮ አራፋት ፣ ኢማኑኤል ፌቮ

ቅዱስ ጊዮርጊስ (8)

ለዓለም ብርሃኑ ፣ አብዱልሪም መሐመድ ፣ ሙሉአለም መስፍን ፣ ጋዲሳ መብራቴ ፣ አሜ መሐመድ ፣ ታደለ መንገሻ ፣ ኢብራሂማ ፎፋና ፣ መሐመድ ኬይታ ሲዴ 

አዳማ ከተማ (7)

ዳንኤል ተሾመ ፣ ከነአን ማርክነህ ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ ፣ አብዱልሀኪም ሱልጣን ፣ አላዛር ፋሲካ ፣ ኢስማኤል ሳንጋሪ

ሀዋሳ ከተማ (7)

ተክለማርያም ሻንቆ ፣ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን ፣ ሳዲቅ ሴቾ ፣ ሙሉአለም ረጋሳ ፣ ላውረንስ ላርቴ ፣ ያቡን ዊልያም ፣ ጋብሬል አህመድ

አርባምንጭ ከተማ (5)

ሲሳይ ባንጫ ፣ ታዲዮስ ወልዴ ፣ ዮናታን ከበደ  ፣ አሌክስ አሙዙ ፣ ላኪ ሳኒ

መከላከያ (2)

አማኑኤል ተሾመ ፣ አቅሌሲያስ ግርማ

ደደቢት (1)

ፋሲካ አስፋው

ውሳኔ የሚጠብቅ፡ አክሊሉ አያናው (ተጫዋቹ ለፋሲል ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ፈርመሀል በሚል የተላለፈለት ቅጣት በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ተሽሮ 20 ሺህ ብር በመክፈል ለቡና እንዲጫወት ተወስኖ ኋላ ላይ ደግሞ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጉዳዩ መያዙን መዘገባችን የሚታወስ ነው::)

– ሰዒዱ ባንሴ (አርባምንጭ) እና ሂላሪ ኢኬና (ወላይታ ድቻ) ዝውውሮች እክል አጋጥሟቸው ሳይጠናቀቁ ቀርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *