​ሴካፋ 2017 | ዋልያዎቹ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ነገ ያደርጋሉ

በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ካፕ ኢትዮጵያ ማክሰኞ በ9፡00 ደቡብ ሱዳንን በመግጠም የምድብ ጨዋታዋን ትጀምራለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ከ4:55 ጀምሮ በካካሜጋ ትምህርት ቤት ሜዳ ልምምዱን ሰርቷል። ዋሊያዎቹ በካካሜጋ ከተማ ሲያ ገስት ሃውስ ከሐሙስ ጀምሮ መቀመጫውን አድርጎ ለሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ዋንጫ የምድብ ሁለት ጨዋታ ዝግጅቱን ቀጥሏል።

ብሄራዊ ቡድኑ ቀለል ያለ ልምምድ ዛሬ ያከናወነ ሲሆን ከተስፋዬ አለባቸው በቀር 22ቱም ተጨዋቾች በልምምዱ ላይ ሲሳተፉ ከጉዳት እያገገመ የሚገኘው አማካዩ ተስፋዬ ለብቻው ቀላል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ተስተውሏል። ነገ ከደቡብ ሱዳን ጋር ላለው ጨዋታም የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ ነው። ቢሆንም ለቀጣዮቹ ጨዋታዎች ግን እንደሚደርስ ይጠበቃል።

ማክሰኞ ህዳር 26

8፡00 – ዛንዚባር ከ ሩዋንዳ (ማቻኮስ)

9፡00 – ኢትዮጵያ ከ ደቡብ ሱዳን (ካካሜጋ)

10፡00 – ኬንያ ከ ሊቢያ (ማቻኮስ)

ሐሙስ ህዳር 28

8፡00 – ታንዛኒያ ከ ዛንዚባር (ማቻኮስ)

9፡00 – ኢትዮጵያ ከ ብሩንዲ (ካካሜጋ)

10፡00 – ሩዋንዳ ከ ሊቢያ (ማቻኮስ)

አርብ ህዳር 29

9፡00 – ዩጋንዳ ከ ደቡብ ሱዳን (ካካሜጋ)

ቅዳሜ ህዳር 30

8፡00 – ሩዋንዳ ከ ታንዛኒያ (ማቻኮስ)

10፡00 – ኬንያ ከ ዛንዚባር (ማቻኮስ)

እሁድ ታህሳስ 1

9፡00 – ኢትዮጵያ ከ ዩጋንዳ (ካካሜጋ)

ሰኞ ታህሳስ 2

8፡00 – ሊቢያ ከ ዛንዚባር (ማቻኮስ)

9፡00 – ደቡብ ሱዳን ከ ቡሩንዲ (ካካሜጋ)

10፡00 – ኬንያ ከ ታንዛኒያ (ማቻኮስ)

የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ዋንጫ በሶከር ኢትዮጵያ እንዲቀርብ ያስቻለው ጎ ቴዲ ስፖርት ነው፡፡ ጎ ቴዲ ስፖርት በኢትዮጵያ የማራቶን ትጥቆች ወኪል አከፋፋይ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *