​ሰላም ዘርዓይ በይፋ የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሆና ተሾመች

የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በቅርቡ ለሚጠብቀው የ2018 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ እና በሩዋንዳ አዘጋጅነት ለሚደረገው የሴካፋ ዋንጫ ዝግጅት አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይን አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ዛሬ በይፋዊ ደብዳቤ ገልጿል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ የሆነችው ሰላም ዘርዓይ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደነበረች የሚታወስ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ የሦስት ወር ቀሪ ኮንትራት የነበራት።

አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ አብረዋት የሚሰሩ አሰልጣኞችን ለፌዴሬሽኑ ያሳወቀች ሲሆን በ17 አመት በታች ቡድን አጋሮቿ የነበሩት ረዳት አሰልጣኙ ብዙአየሁ ዋዳ (ልደታ ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ) እና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙ ውብሸት ደሳለኝ (የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ) ናቸው።

አሰልጣኝ ሰላም እና አጋሮቿ ስራቸውን በቅርቡ ባይጀምሩም እስከ አንደኛው ዙር የሴቶች ፕሪምየር ሊግ መጠናቀቅ ድረስ ተጫዋቾችን በክልል እና በአአ በሚደረጉ ጨዋታዎች የመምረጥ እና የመገምገም ስራ እንደሚሰሩ እንዲሁም በቀጣይ የውድድሮቹ የሚካሄዱበት ቀናት ሲቃረብ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገቡ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *