ፋሲል ከተማ አምስት ተጫዋቾቹን አስጠንቅቋል

ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው የሚሰጡት ማስጠንቀቂያ ቀጥሎ ፋሲል ከተማም ለሁለት የውጭ ዜጎች እና ለሦስት የሀገር ውስጥ ተጨዋቾቹ የማስጠንቀቂ ደብዳቤ መስጠቱ ታውቋል።

ፋሲል ከነማ በዘንድሮ አመት እንዳካሄደው ከፍተኛ የዝውውር እንቅስቃሴ አንፃር ደጋፊው በሚተማመንበት መልኩ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ አይገኝም። ክለቡም ለቡድኑ ጥሩ አቋም እያሳያችሁ አይደለም ፣ ራሳችሁን ማሻሻልም ይገባቸዋል ያላቸው አምስት ተጨዋቾችን በደብዳቤ አስጠንቅቋል። 

ክለቡ ያስጠነቀቃቸውን ተጫዋቾች ማንነት ከመግለፅ ቢቆጠብም ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ ዩጋንዳዊው ሮበርት ሴንቶንጎ ፣ ናይጄርያዊው ፊሊፕ ዳውዝ ፣ ግብ ጠባቂው ቢንያም ሀብታሙ ፣ ተከላካዩ አቤል ውዱ እና የመስመር አጥቂው ናትናኤል ጋንቹላ መሆናቸው ተነግሯል። የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከደረሳቸው መካከልም አቤል እና ሮበርት ከክለቡ ጋር በስምምነት ሊለያዩ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

በተያያዘ ዜና ፋሲል ከተማ በሁለተኛው ዙር የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ በዝውውሩ ላይ ለመሳተፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ሊያመጣ እንደሚችል ሰምተናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *