​ፌዴሬሽኑ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ የጣለውን ቅጣት ይፋ አደረገ

በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን አስተናግዶ አቻ ሲለያይ በጨዋታው መገባደጃ ላይ በተከሰቱ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለቶች ዙርያ የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ያሳለፈውን የቅጣት ውሳኔ ለክለቦቹ እና ለመገናኛ ብዙሀን ይፋ አድርጓል።

በጨዋታው 86ኛ ደቂቃ ላይ በግራ የካታንጋ ክፍል ቁሶችን በመወርወር የተጀመረው ግርግር ለ28 ደቂቃ ጨዋታውን አቋርጦ እየተባባሰ በመምጣት ደጋፊዎችን ለጉዳት ወደዳረገ ረብሻ መሸጋገሩ የሚታወስ ሲሆን ለክስተቱ ተጠያቂ የተደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 180 ሺህ ብር ቅጣት ፣ የንብረት ጉዳት ወጪ እና የተጎዱ ደጋፊዎች የህክምና ወጪ እንዲሸፍን እንዲሁም አንድ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ ተወስኖበታል። ሆኖም ፌዴሬሽኑ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ አልገለፀም።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ በተጨማሪ የእንግዳው ቡድን አዳማ ከተማ ደጋፊዎች የረብሻው አካል በመሆናቸው የ25 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *