​ኒጀር 2019፡ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆነ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ በሚቀጥለው አመት በኒጀር ይካሄዳል፡፡ የማጣሪያ ጨዋታዎቹ በመጋቢት ወር ሲጀምሩ ኮንፌድሬሽኑም ድልድሉን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

በማጣሪያው የምትሳተፈው ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር ከቡሩንዲ ጋር ተደልድላለች። የመጀመሪያውን ጨዋታ ኢትዮጵያ በሜዳዋ የምታደርግ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት አሸናፊ ከሱዳን ጋር በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ይገናኛል፡፡ በመጨረሻው ዙር ማጣሪያ አላፊ የሚሆነው ሃገር ኬንያ ከ ሩዋንዳ እና የዛምቢያን አሸናፊ ይገጥማል፡፡

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በ2017 ዛምቢያ ባስተናገደችው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ማለፍ ሳይችል በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ተሸንፎ ወድቋል፡፡ ኢትዮጵያ በቅደመ ማጣሪያው ሶማሊያን 4-1 በአጠቃላይ ውጤት ብታሸንፍም በጋና በድምር ውጤት 5-2 ተሸንፋ ከማጣሪያው ውጪ መሆኗ ይታወሳል፡፡ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ ግርማ ሃብተዮሃንስ የነበሩ ሲሆን አሁን ለሚመጣው ማጣሪያ ብሄራዊ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ እንደሚቀጠርለት ይጠበቃል፡፡

አንጎላ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሮን፣ ኮንጎ፣ ኮትዲቯር፣ ጋምቢያ፣ ጋና፣ ጊኒ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካ እና የወቅቱ ቻምፒዮን ዛምቢያ በቀጥታ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲሻገሩ አዘጋጇን ኒጀርን ጨምሮ 7 ሃገራት በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ሙሉ ድልድል

አንደኛ ዙር

(የመጀመሪያ ጨዋታ ከመጋቢት 21-23 ባሉት ቀናት) (የመልስ ጨዋታ ከ ሚያዚያ 12-14 ባሉት ቀናት)

ሞሪታንኒያ ከ ሞሮኮ

ጊኒ ቢሳው ከ ሴራ ሊዮን

አልጄሪያ ከ ቱኒዚያ

ላይቤሪያ ከ ቤኒን

ጋቦን ከ ቶጎ

ኬንያ ከ ሩዋንዳ

ኢትዮጵያ ከ ቡሩንዲ

ዩጋንዳ ከ ደቡብ ሱዳን

ታንዛኒያ ከ ዲ.ሪ. ኮንጎ

ሲሸልስ ከ ሞዛምቢክ

ማላዊ ከ ስዋዚላንድ

ቦትስዋና ከ ናሚቢያ

ሁለተኛ ዙር

(የመጀመሪያ ጨዋታ ከግንቦት 3-5 ባሉት ቀናት)

(የመልስ ጨዋታ ከግንቦት 10-12 ባሉት ቀናት)
የሞሪታንኒያ እና ሞሮኮ አሸናፊ ከ ጊኒ

የጊኒ ቢሳው እና ሴራ ሊዮን አሸናፊ ከ ናይጄሪያ

የአልጄሪያ እና ቱኒዚያ አሸናፊ ከ ጋና

ጋምቢያ ከ ላይቤሪያ እና ቤኒን አሸናፊ

ቡርኪና ፋሶ ከ ሊቢያ

የጋቦን እና ቶጎ አሸናፊ ከ ኮንትዲቯር

የኬንያ እና ሩዋንዳ አሸናፊ ከ ዛምቢያ

የኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ አሸናፊ ከ ሱዳን

የዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን አሸናፊ ከ ካሜሮን

የታንዛኒያ እና ዲ.ሪ. ኮንጎ አሸናፊ ከ ማሊ

የሲሸልስ እና ሞዛምቢክ አሸናፊ ከ ደቡብ አፍሪካ

የማላዊ እና ስዋዚላንድ አሸናፊ ከ አንጎላ

የቦትስዋና እና ናሚቢያ አሸናፊ ከ ኮንጎ ሪፐብሊክ

ሴኔጋል ከ ግብፅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *