ሉሲ | ሰላም ዘርዓይ 11 ተጫዋቾችን ቀነሰች

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ2019 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ከመረጠቻቸው 36 ተጫዋቾች መካከል 11 ተጫዋቾችን በመቀነስ የመጨረሻዎቹ 25 ተጫዋቾችን አሳውቃለች።

ሉሲዎቹ ከሊቢያ ጋር ለሚያደርጉት የመጀመርያ ዙር የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ተጠርተው ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል ገነት አክሊሉ ፣ ሽብሬ ካንቦ ፣ እፀገነት ብዙነህ ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ ፣ መዲና ጀማል ፣ አለምነሽ ገረመው ፣ ሜላት ደመቀ ፣ ልደት ቶላ ፣ ቤቴልሄም ሰማን ፣ ፎዝያ መሐመድ እና ትዝታ ፈጠነ የተቀነሱ ተጫዋቾች ናቸው።

የመጨረሻ 25 ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ማርታ በቀለ (መከላከያ) ፣ አባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ትዕግስት አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ተከላካዮች
መሠሉ አበራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፀጋነሽ ተሾመ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ዘለቃ አሰደፋ (ደደቢት) ፣ ብዙአየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቤተልሄም ከፍያለው (ኤሌክትሪክ) ፣ መስከረም ካንኮ (ደደቢት) ፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ገነሜ ወርቁ (ጌዴኦ ዲላ)

አማካዮች

ሠናይት ቦጋለ (ደደቢት) ፣ አረጋሽ ልኬሳ (አካዳሚ) ፣ ዙሌይካ ጁሀድ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ቤዛዊት ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ ብሩክታዊት ግርማ (ደደቢት)

አጥቂዎች

ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ትዕግስት ዘውዴ (ደደቢት) ፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከተማ) ፣ ሲሳይ ገብረወልድ (አካዳሚ)

ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን ከየካቲት 27 ጀምሮ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታቸውን ከሊቢያ ጋር ከሜዳቸው ውጪ ከመጋቢት 22 እስከ 24 ባሉት ቀናት ያደርጋሉ። የመልሱን ጨዋታ አአ ላይ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሲያደርጉ ይህን ዙር ካለፉም በቀጣይ የማጣርያ ዙር የሴኔጋል እና አልጄርያ አሸናፊን የሚገጥሙ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *