ተመስገን ዳና የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

በታንዛንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2019 የአፍሪካ የ17 አመት በታች ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎችን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተመስገን ዳናን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ታውቋል። 

የሀዋሳ ከተማ ከ20 አመት በታች ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ተመስገን ባለፉት አመታት በወጣቶች እግርኳስ ላይ ስኬታማ ከሆኑ አሰልጣኞች መካወል ግንባር ቀደሙ ነው። በ2008 ከ17 አመት በታች ቡድኑ ጋር የጥምር ዋንጫ አሸናፊ ሲሆን በ2009 ወደ 20 አመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝነት ተሸጋግሮ በድጋሚ ባለድል መሆን ችሏል።

ለ2017 ወድድር የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታ ላይ ደርሶ በማሊ 4-1 ተሸንፋ ከውድድር ውጪ የሆነው ከ17 አመት በታች ቡድኑ ቀጣይ የማጣርያ ተጋጣሚዎች በቅርቡ የሚታወቁ ሲሆን በግንቦት ወር ጨዋታ ይጀምራል። ካፍ ባሳለፍነው ክረምት በወሰነው ውሳኔ መሰረት ሀገራት በየዞናቸው (ክፍለ አህጉር) የማጣርያ ጨዋታ አድርገው ወደ ውድድሩ እንደሚያልፉ ማሳወቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከ1997 (እኤአ) በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ለውድድር የመቅረብ የተሻለ እድል ተፈጥሮላታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *