ምንያምር ጸጋዬ ከመከላከያ አሰልጣኝነት ተነሱ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር ዘመን 13ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ መልካም ያልሆነ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው መከላከያ ዋና አሰልጣኙ ምንያምር ጸጋዬን ከኃላፊነት ማንሳቱ ታውቋል።

በአመቱ መጀመርያ አሰልጣኝ በለጠ ገብረኪዳንን ተክቶ በዋና አሰልጣኝነት የተሾሙ ቢሆንም በክለቡ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማስመዝገብ ባለመቻላቸው እና በቅርብ ጊዜያትም መሻሻል ባለመቻሉ አሰልጣኙ እንዲሰናበተለ መወሰኑን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መከላከያ አሰልጣኙን ማሰናበቱን ተከትሎ ከሰበታ ከተማ ጋር በስምምነት የተለያዩት አሰልጣኝ ስዩም ከበደን ለመሾም ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *