የሴካፋ ሴቶች ቻምፒየንሺፕ በሩዋንዳ ይካሄዳል

የሴካፋ ሴቶች ቻምፒየንሺፕ በግንቦት ወር በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ሴካፋ አረጋግጧል፡፡ ተሳታፊ ሃገራት ሙሉ ለሙሉ ባልታወቁበት ውድድር ላይ ኢትዮጵያ እንደምትሳተፍ ይጠበቃል፡፡

ውድድሩ ከግንቦት 4-12 እንደሚደረግ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ሲሆን በ2016 ዩጋንዳ አስተናግዳ ታንዛኒያ አሸናፊ መሆን መቻሏ ይታወሳል፡፡ ሉሲዎቹ በ2016 ውድድር ተሳትፈው ሶስተኛ ደረጃን ያገኙ ሲሆን በዘንድሮው ውድድር ላይ መሳተፋቸው ለመጪው የቶታል አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ጥቅም እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

ሴካፋ በሴቶች እና ታዳጊዎች ውድድር ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት በአባል ሃገራት መካከል መግባባት ላይ ከተደረሰ በኃላ የ17 ዓመት በታች ዋንጫን ቡሩንዲን ስታስተናግድ ሩዋንዳ ደግሞ የሴቶች ዋንጫን ታዘጋጃለች፡፡ የካጋሜ ክለቦች ውድድርም በክረምቱ ወር ታንዛኒያ ላይ እንደሚስተናገድ ይጠበቃል፡፡

ለውድድሩ ሩዋንዳ ለ2016 የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒየንሺፕ (ቻን) ጨዋታዎችን ያስተናገዱ ስታዲየሞችነረ እንደምትጠቀም ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *