ፋሲል ከተማ አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡን ሲያሰናብት መሳይ ተፈሪን ቀጥሯል

ፋሲል ከተማ አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ እና ምክትሉን ተገኝ እቁባይ ማሰናበቱ ታውቋል፡፡ የጎንደሩ ክለቡ ቦርድ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የቀድሞ የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ቀጣዩ የክለቡ አሰልጣኝ እንዲሆንም ወስኗል፡፡ ክለቡ በአመቱ መጀመሪያ ነበር አሰልጣኝ ምንተስኖትን በቋሚነት የቀጠረው፡፡

አሰልጣኝ ምንተስኖት ከ2009 የውድድር ዘመን አጋማሽ የቀድሞ አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ ከክለቡ ጋር ከተለያዩ ጀምሮ አፃዎቹን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን በያዝነው ዓመት በደጋፊዎች በሚቀርብባቸው ትችቶች እና ተቋውሞች ጋር የያዙት ቡድን 26 ነጥቦችን ሰብስቦ በደረጃ ሰንጠረዡ 7ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አፃዎቹ አምና ከነበራቸው እንቅስቃሴ የወረደ አቋም ላይ መገኘታቸውን ተክተሎ ክለቡ የአሰልጣኝ ለውጡን ለማድረግ መገደዱ ታውቋል፡፡ ፋሲል በአሰልጣኝ ምንተስኖት ቆይታ ላይ ሲወስን ይህ ለመጀመሪያ ግዜ አይደለም፡፡ የምንተስኖት ምክትል የነበረው ተገኝ እቁባይም በተመሳሳይ ከስራቸው ተሰናብተዋል፡፡ ፋሲል ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ያለግብ አቻ የተለያየበት ጨዋታ ለሁለቱም አሰልጣኞች የመጨረሻቸው ሆኗል፡፡

ፋሲል አዲሱን አሰልጣኝ ለመቅጠር ግዜ የፈጀ አይመስልም፡፡ ወላይታ ድቻን ከምስረታው ጅምሮ ያሰለጠኑት እና ከሶዶው ክለብ ጋር በያዝነው አመት የተለያዩት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ አዲሱ የፋሲል ከተማ አሰልጣኝ መሆናቸው ታውቋል፡፡ አሰልጣኝ መሳይ ስማቸው ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ሲያያዝ ቆይቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *