ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ካራ ብራዛቪል | የአሰልጣኞት አስተያየት

የ2018 ቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች በተለያዩ ሀገራት ተካሂደዋል። አዲስ አበባ ላይ ካራ ብራዛቪልን ያሰተናገደው የኢትዮጵያው ቻምፒየን ቅዱስ ጊዮርጊስም 1-0 አሸንፏል። ከጨዋታው በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች የሰጡትን አስተያየት እነሆ::

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ
ስለ ጨዋታው 

ጊዮርጊስ የበለጠ አጥቅቶ ነው የተጫወተው ጨዋታውን የበለጠ ተቆጣጥረን ተጫውተናል በተለይ ሁለተኛ ግማሽ የበለጠ ተጭነን ተጫውተናል ሁለት ሶስት ግብ የማግባት አጋጣሚዎችን ፈጥረን ነበር ማግባት የቻልነው ግን አንድ ብቻ ነው በእንደዚ አይነት ውድድሮች ዋናውና አስፈላጊው ነገር ጎል ማግባትና ጎል እንዳይገባብህ መከላከል ነው ሁለቱንም አሳክተናል ስለዚህ ለቀጣ ጨዋታ ደግሞ እንዘጋጃለን በእግር ኳስ እሚፈጠረውን አታውቅም የበለጠ መጠንከር የበለጠ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅብናል  የሚቀጥለው ጨዋታ በብራዛቪል ነው ዋናው ነገር ግብ አልተቆጠረብንም

ስለ ጨዋታ ዕቅድ

ክለቡን በሚገባ አውቀዋለው፤ ለተጫዋቾቼም ሰሞኑን እየነገርኳቸው ነበር የሚመጡት ቢበዛ አቻ ለመውጣት ነው እየተባባልን ነበር በመልሶ ማጥቃት በተለይ በ11 ቁጥሩና በ17 ቁጥሩ በኩል እንደሚጫወቱ አስበን ተዘጋጅተን ነበር በመጀመያው 45 ደቂቃ ጎል ማስቆጠር አለብን ተባብለን ነበር፤ አልሆነም በሁለተኛው አጋማሽ ሁለተኛውን ዕቅዳችን ሞከርን አዳነን ወደሜዳ አስገባን አማራጭ እቅዳችን ስለሰራ በጣም ደስተኞች ነን።

ስለ መልስ ጨዋታ
የበለጠ ጠንካራ ጨዋታ እጠብቃለው የመጨረሻ ሁለት ጨዋታቸውን ከጋናው ኮቶኮና ከቱኒዚያው ጋር ያደረጉትን ጨዋታዎች በሚገባ ተመልክተናል ከዚህ በፊት ያሰለጠንኳቸው ኮንጎአዊ ተቻዋቾችም ነበሩኝ፡፡ በሚገባ አውቃቸዋለው፤ በተጨማሪ ይህንንም ጨዋታ በሚገባ እንገመግማለን፤ ለመልሱ ጨዋታ በሚገባ እንዘጋጃለን፡፡ ነገር ግን አሁን ከፊታችን ቅድሚያ ከሲዳማ ቡና ጋር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አለብን፡፡ ቅድሚያ የምንሰጠው ከሲዳማ ጋር ላለብን ጨዋታ ነው ከሲዳማው ጨዋታ በኋላ በመጪው ሳምንት ለመልሱ ጨዋታ እንዘጋጃለን፡፡

የካራ ብራዛቪሉ አሰልጣኝ ሮጀር ኤሊ ኦሲዬት

ስለ ጨዋታው

ከፍተኛ የቴክኒክ ደረጃ የታየበት ጨዋታ ነበር፤ ተጋጣሚየችንን ማድነቅ እፈልጋለው፡፡ የቴክኒክ ደረጃቸው ላቅ ያለ ነው፤ በሁለታችንም በኩል ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ ነበር፤ በትኩረት ማጣት ከገባብን አንድ ጎል በቀር በጣም ጥሩ ጨዋታ ተጫውተናል፤ ጎሉም ቢሆን ለኛ መማሪያ ነው፡፡ ለመልሱ በሚገባ እንድንዘጋጅ ያደርገናል፤ ውድድሩ ገና አላለቀም፤ የመልስ ጨዋታ ይቀረናል፡፡

ስለ ውጤቱ

አንድ ጎል ነው የተቆጠረብን ስንመጣ  ያለምንም ጎል ባዶ ለባዶ፣ ወይም አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ለመመለስ ነበር ሃሳባችን፤ አልተሳካም፡፡ አንድ ጎል ተቆጠረብን፡፡ የኛ አጥቂ ሁለት ሦስት እድሎችን ተፈጥሮለት መጠቀም አልቻለም፡፡ በተለይ አንዱን አጋጣሚ መጠቀም ነበረበት፤ አልተጠቀመበትም፡፡ ሜዳውም ትንሽ አሰቸጋሪ ነበር ስለዚህ አልቻለም፡፡ አሁን ተጋጣሚያችን በደንብ አይተናል፣ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በደንብ ታዝበናል፣ ከጨዋታው በመነሳት ለመልሱ ጨዋታ በሚገባ እንዘጋጃለን፡፡

ስለ መልስ ጨዋታው

አምና ሌዎፓርድን ይዤ ስመጣ ሁለት ለምንም ነበር የተሸነፍነው፤ አሁን አንድ ለባዶ ነው፡፡ መሻሻሎች አሉን ማለት ነው አሁንም የቀሩ ድክመቶቻችንን አርመን ከዚ የበለጠ ጠንክረን በሜዳችን ሁለትና ከዚያ በላይ አግብተን እናልፋለን፡፡

በውጤቱ የተሰማቸው ስሜት

በውጤቱ አላዘንኩም፤ ይህ እግር ኳስ ነው በእግር ኳስ ማሸነፍ፣ መሸነፍና፣ አቻ መውጣት የግድ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ተሸንፈናል፤ ነገር ግን የመልስ ጨዋታ ደግሞ አለ፡፡ የበለጠ እንዘጋጃለን፤ እናሸንፋለን ከሁለት በላይ ግብ አስቆጥረን ወደምድብ ማጣሪያው እናልፋለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *