ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ | ፈረሰኞቹ ለመልሱ ጨዋታ ነገ ወደ ኮንጎ ያቀናሉ

የ2018 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታቸውን አዲስ አበባ ስታድም ላይ የኮንጎ ሪፐብሊኩ ካራ ብራዛቪልን አስተናግዶ 1-0 ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመልሱ ጨዋታ ነገ ወደ ብራዛቪል ይበራል።

የመልሱን ጨዋታ የፊታችን ረቡዕ የሚያደርጉት ፈረሰኞቹ ዛሬ የመጨረሻ ልምምዳቸውን ያከናወኑ ሲሆን ከጨዋታው ከሚደረገደበት አራት ቀን አስቀድመው ነገ ማለዳ 18 ተጨዋቾችን በመያዝ ወደ ጎንጎ የሚያቀኑ ይሆናል። በጉዳት/ቅጣት ከመጀመርያው ጨዋታ ውጪ የነበረው አስቻለው ታመነ ከቡድኑ ስብስብ ውስጥ ተካቶ የሚጓዝ ይሆናል።
የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ አስፈላጊውን ውጤት ይዘው ለመመለስ እንደተዘጋጁ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ” ቡድኑ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ የሚባል  ተነሳሽነት እና በራስ መተማመን አለ። ለጨዋታውም በሚገባ ዝግጅት አድርገናል ። የምንሄደው ለማሸነፍ ነው ፤ አሸንፈን ለሀገራችንም ሆነ ለደጋፊዎቻችን አንድ ነገር ሰርተን እንመለሳለን። ” ብለዋል።

ወደ ብራዛቪል የሚያመሩት 18 ተጨዋቾች ስም ዝርዝር

ግብጠባቂ ፡ ሮበርት ኦዶንካራ ፣ ለዓለም ብርሃኑ ፣

ተከላካዮች ፡  አስቻለው ታመነ ፣ ሳላዲን በርጌቾ ፣ ደጉ ደበበ ፣ መሀሪ መና ፣ አበባው ቡጣቆ ፣ አብዱልከሪም መሀመድ ፣ ፍሬዘር ካሳ

አማካዮች ፡ ሙሉዓለም መስፍን ፣ ምንተስኖት አዳነ ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ ፣ ጋዲሳ መብራቴ ፣ በኃይሉ አሰፋ

አጥቂዎች ፡ አዳነ ግርማ ፣ አሜ መሀመድ ፣ አቡበከር ሳኒ