ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢብራሂማ ፎፋና ተለያዩ

ባለፈው ዓመት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ክለብ ያሳየውን ድንቅ አቋም ተከትሎ በዘንድሮው ዓመት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከፈረሙት አምስት ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ኮትዲቯራዊው ኢብራሂማ ፎፋና ከወራት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

ተጫዋቹ በውድድር ዓመቱ ከቡድኑ ጋር ለመዋሀድ ሲቸገር የተስተዋለ ሲሆን እያሳየ ያለው አቋም የቅዱስ ጊዮርጊስን አሰልጣኝ ቫዝ ፒንቶን ስላላሳመናቸው ከቡድኑ ዝርዝር ውጭ ሆኖ ቆይቷል፤ ሆኖም ከአሰልጣኙ ጋር የነበረውን ልዩነት ፈትቶ በድጋሚ ልምምድ ቢጀምርም በአሁኑ ወቅት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሙሉ በሙሉ መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ከወኪሉ  አረጋግጣለች፡፡ ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር የተለያየው ከአሰልጣኙ ጋር በታክቲካዊ ጉዳዮች ባለመስማማት ብቻ መሆኑን የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ እንዲሁም የተጫዋቹ ወኪል አቶ ላሚን ዲያሎ ከኮትዲቯር ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡

ከኮትዲቯራዊው አጥቂ በቀጣይ የቀድሞ ክለቡ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ዳግመኛ ሊቀላቀል እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።