ሰበር | የኢትዮጵያ ዳኞች እና ታዛቢዎች ለ3 ሳምንት ውድድሮች ላለመዳኘት ወሰኑ

የኢትዮጵያ ዳኞች እና ታዛቢዎች ማኅበር ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ለተፈጠሩ ችግሮች ተግባራዊ እርምጃዎች እስኪወስድ ከነገ ጀምሮ ለቀጣዮቹ 3 ሳምንታት ማንኛውም በፌዴሬሽኑ ስር የሚካሄዱ ውድድሮችን ላለመዳኘት ከውሳኔ ላይ ደርሷል።

ማኅበሩ በዛሬው ጠቅላላ ጉባዔ እንዲተገበሩ ያላቸውን እነዚህን አስር ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጧል፡-
1ኛ. በ2010ዓ.ም የውድድር ዘመድ የተጎዱ ዳኞቻችን ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸው።
2ኛ.ውድድሩን ከመጀመራችን በፊት በውድድር ደንቡ መሰረት ኢንሹራንስ እንዲኖርልን።
3ኛ.ረዳት ዳኛ ሙስጠፋ መኪ በሃገር ውስጥም ሆነ ውጪ ተገቢውን ህክምና እንዲደረግለት።
4ኛ.ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመግባባት የዳኞች ጥበቃ እንዲያደርግልን።
5ኛ.በወንዶች እና በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ለመዳኘት የጉዞ ውቅት አውሮፕላን የሚደርስበት ቦታ ሁሉ ትራንስፓርት እንዲመቻችልን።
6ኛ.የእያሱ ፈንቴን ጉዳይ ጨምሮ ፖሊስ ያወቃቸው የስርዓት አልበኝነት የመብት ጥሰቶች ተገቢውን የህግ ፍርድ እንዲያገኙ እንዲደረግ።
7ኛ. ፌዴሬሽኑ ለዳኞች እና ለታዛቢዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲመቻች።
8ኛ. ማህበሩ ያለአግባብ ለጠቅላላ ጉባኤ ያወጣው ወጪ በፌዴሬሽኑ በህጋዊ ደረሰኝ አማካኝነት እንዲመለስ።
9.የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎቹ አስራር በግልፅ እንዲጠየቅልን።
10.ተገቢው የህግ ከለላ በሌለባቸው ስታዲየሞች ውድድር እንዳይካሄድ።