ፌዴሬሽኑ ከዳኞች ጋር ከስምምነት ላይ ከደረሰ የተቋረጠው ፕሪምየር ሊግ በተስተካካይ ጨዋታዎች ይቀጥላል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተቋረጠው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቀጣይ ሳምንት በተስተካካይ መርሀ ግብር እንደሚቀጥል አስታወቀ። የዳኞች እና ታዛቢዎች ማኅበር ማናቸውንም ውድድሮች እስከ ግንቦት 20 ድረስ እንደማይዳኝ ማሳወቁ የሚታወስ ሲሆን በሁለቱ ወገኖች መካከል በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ የሚገኘው ስብሰባ በስምምነት ከተጠናቀቀ ተስተካካይ ጨዋታዎቹ ከሰኞ ግንቦት 6 ጀምሮ ይካሄዳሉ ሲል ፌዴሬሽኑ ለክለቦች በተላከ ደብዳቤ ገልጿል።

በአፍሪካ ውድድር ምክንያት ያልተደረጉት እና በስርዓት አልበኝነት ምክንያት ያልተጠናቀቀው ጨዋታ ይካሄድባቸዋል የተባሉት ቀናት የሚከተሉት ናቸው።

ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010 

09:00 ወልዋሎ ከ መቐለ ከተማ (ሽረ ፤ 45 ደቂቃ)

09:00 አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ (አዳማ)

10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኤሌክትሪክ (አአ)

ዓርብ ግንቦት 10 ቀን 2010 

09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ (ድሬዳዋ)

09:00 መቐለ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (መቐለ)