የፕሪምየር ሊጉ 23ኛ ሳምንት የሚደረግበት ቀን ታውቋል

ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሰኞ እና ዓርብ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀምራል። ከተስተካካይ መርሀ ግብር በኋላ መደበኛ ጨዋታዎች መቼ እንደሚካሄዱም ታውቋል።

የ23ኛ ሳምንት ውድድር በሙሉ ረቡዕ ግንቦት 13 የሚካሄድ ይሆናል። በዚህም መሠረት :-

ረቡዕ ግንቦት 15 ቀን 2010

08:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዋሎ (አአ ስታድየም)

09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ መከላከያ (ድሬዳዋ)

09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ (ሀዋሳ)

09:00 አዳማ ከተማ ከ መቐለ ከተማ (አዳማ)

09:00 ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና (ሶዶ)

09:00 ወልዲያ ከ ኢትዮጵያ ቡና (ሰበታ)

09:00 ጅማ አባጅፋር ከ አርባምንጭ ከተማ (ጅማ)

10:00 ደደቢት ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (አአ)

ውድድሩ ከሰኔ 30 በፊት እንዲጠናቀቅ በሚመስል መልኩ በየ5 ቀናት ልዩነቶች ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን በታሰበው መልኩ የሚካሄድ ከሆነ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሰኔ 30 የሚካሄዱ ይሆናል። ሙሉውን የውድድር ፕሮግራም ለአጠቃቀም በሚመች መልኩ እስክናዘጋጅ ድረስ የጨዋታ ሳምንቶች የሚካሄዱባቸው ጊዜያት የሚከተሉት ናቸው።

24ኛ ሳምንት – ግንቦት 20 እና 21

25ኛ ሳምንት – ግንቦት 25 እና 26

26ኛ ሳምንት – ግንቦት 30 ፣ ሰኔ 1 እና 2

27ኛ ሳምንት – ሰኔ 6 እና 7

28ኛ ሳምንት – ሰኔ 12 እና 15

29ኛ ሳምንት – ሰኔ 21

30ኛ ሳምንት – ሰኔ 28፣ 29 እና 30