ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረግ ጨዋታ ይጀምራል

በብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ እኛ ዝግጅት ምክንያት ከአንድ ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን ከዛሬ ጀምሮ በሚደረጉ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ይጀምራል።

ዛሬ አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ በ09:00 አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳል። ሁለቱም ቡድኖች ከዋንጫ ፉክክሩ የራቁ ቢሆንም ከወራጅ ቀጠናው ያላቸው የነጥብ ልዩነት ጥቂት ከመሆኑ አንፃር ይህ ጨዋታ ወሳኝ ነው።

የ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን መርሐ ግብር ይህን ይመስላል:-

ሀሙስ ሰኔ 7 ቀን 2010

09:00 አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ (አዳማ)

አርብ ሰኔ 8 ቀን 2010

09:00 ጌዴኦ ዲላ ከ መከላከያ (ዲላ)

ቅዳሜ ሰኔ 9 ቀን 2010

08:00 ኢት.ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ (ባንክ ሜዳ)

08:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና (አአ ስታድየም)

10:00 ደደቢት ከ ድሬዳዋ ከተማ (ባንክ ሜዳ)