በሁለት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጓል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲካሄዱ ቅዳሜ አዲስ አበባ ስታድየም የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጓል።

ወልዲያ ላይ በተላለፈው ቅጣት መሠረት አዲስ አበባ ላይ ቅዳሜ 09:00 እንዲካሄድ መርሐ ግብር የወጣለት የወልዲያ እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ ረፋድ 04:00 ላይ የሚከናወን ሲሆን የተሰጠው ምክንያት 08:00 የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መርሐ ግብር አስቀድሞ የወጣ በመሆኑ ነው ተብሏል።

ቅዳሜ 11:30 መርሐ ግብር የወጣለት የደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ወደ 10:00 ተሸጋሽጓል። ከዚህ ጨዋታ በፊት ደግሞ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና መካከል የሚካሄድ ይሆናል።
በተያያዘ ዜና ወላይታ ድቻ ቀጣይ የሜዳውን መርሐ ግብር ቦዲቲ ላይ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ ፌዴሬሽኑ በመቀበሉ ከወልዋሎ የሚያደርገው ጨዋታ ቦዲቲ ላይ የሚከናወን ይሆናል።


የ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር


ቅዳሜ ሰኔ 9 ቀን 2010

04:00 ፋሲል ከተማ ከ ሲዳማ ቡና (ጎንደር)

04:00 ወልዲያ ከ ጅማ አባጅፋር (አአ)

09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኤሌክትሪክ (ድሬዳዋ)

09:00 ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ (ቦዲቲ)

09:00 መቐለ ከተማ ከ መከላከያ (መቐለ)

10:00 ደደቢት ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አአ)


እሁድ ሰኔ 10 ቀን 2010

09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (ሀዋሳ)

09:00 አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ (አዳማ)