የኢትዮጵያ ዋንጫ መርሐ ግብር ላይ ለውጥ ተደርጓል

ከዛሬ ጀምሮ እንደሚካሄድ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ዋንጫ መርሐ ግብር ላይ ፌዴሬሽኑ ለውጥ አድርጓል። አንድ ጨዋታም ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል።

ዛሬ እንዲካሄዱ ታስበው የነበሩት የመከላከያ እና ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም የኤሌክትሪክ እና መቐለ ከተማ ጨዋታ ወደ ነገ ተሸጋግረዋል። በዚህም መሰረት ነገ 04:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያ ከድሬዳዋ ከተማ ሲጫወቱ 09:00 ላይ ኤሌክትሪክ ከ መቐለ ከተማ የረጫወታሉ። 11:30 ላይ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይቻ ድቻ አስቀድሞ በተያዘው ሰዓት መሰረት የሚጫወቱ ይሆናል። 

በአንደኛው ዙር ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ቡድኑን በጊዜያዊነት በመበተኑ ምክንያት ባቀረበው ጥያቄ ወደ ሌላ ጊዜ ሲሸጋገር አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ በተያዘለት መርሐ ግብር መሰረት እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ቡና በዚህ ጉዳይ ላይ ትላንት ቅሬታውን ማቅረቡ የሚታወስ ነው።