ጅማ አባጅፋር በቀጣይ ሳምንት መርሐ ግብር ላይ ቅሬታውን አሰምቷል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይፋ ሲደረግ ለዋንጫው ከሚፎካከሩት ክለቦች አንዱ የሆነው ጅማ አባጅፋር በጨዋታዎቹ ሰዓት ላይ ቅሬታውን አሰምቷል። 

ክለቡ በቅሬታ ደብዳቤው ከጅማ ጋር ለዋንጫ እየተፎካከሩ ከሚገኙት ክለቦች ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ሊጫወት ሲገባ ቀድሞ እንዲጫወት መደረጉ አግባብ እንዳልሆነ ገልጿል። ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ የላከው ደብዳቤ ይህንን ይመስላል።

የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር 

ቅዳሜ ሰኔ 23 ቀን 2010

04:00 መከላከያ ከወልዲያ (አአ)

09:00 ጅማ አባጅፋር ከ ደደቢት (አዳማ)

09:00 ወልዋሎ ከ አዳማ ከተማ (ዓዲግራት)

09:00 አርባምንጭ ከ ሀዋሳ ከተማ (አርባምንጭ)

09:00 ኤሌክትሪክ ከ ፋሲል ከተማ (አአ)

09:00 ሲዳማ ቡና ከ መቐለ ከተማ (ይርጋለም)

11:30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ (አአ)

እሁድ ሰኔ 24 ቀን 2010

10:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (አአ)