በ28ኛው ሳምንት መርሀ ግብር ላይ ለውጥ ተደርጓል

የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ እንደሚደረጉ ይጠበቁ የነበሩት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ ሰኞ ድረስ ተሻግሽገዋል።

ከ25ኛው እና 27ኛው ሳምንት በተዘዋወሩ ተስተካካይ ጨዋታዎች ምክንያት በአንድ ሳምንት የተራዘሙት የሊጉ የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሽግሽግ ተደርጎባቸዋል። ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የተቀመጠው ደግሞ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ሀላፊነት አልወስድም በማለቱ ምክንያት ወደ ነገ የተዘዋወሩት ሁለት ጨዋታዎች ናቸው። በዚህም መሰረት የጨዋታ መደራረብን ለመቀነስ በማሰብ የኢትዮጵያ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ ወደ ሰኞ የተሸጋገረ ሲሆን መከላከያ እና ወልዲያ የሚያደርጉት የሳምንቱን የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዳሜ የሚከናወን ይሆናል። የተቀሩት ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ እንደሚደረጉ ይጠበቃል።

የተሻሻለው መርሀ ግብር ይህን ይመስላል

ቅዳሜ ሰኔ 23 2010

09፡00 መከላከያ ከ ወልዲያ

እሁድ ሰኔ 24 2010

09፡00 ጅማ አባ ጅፋር ከ ደደቢት
09፡00 ወልዋሎ ዓ.ዩ ከ አዳማ ከተማ
09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
09፡00 ሲዳማ ቡና ከ መቐለ ከተማ
09፡00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ፋሲል ከተማ
11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ

ሰኞ ሰኔ 25 2010

10፡00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ