የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሊቀጠርለት ነው

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ታህሳስ 17 ከብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው ከተነሱ በኋላ ላለፉት ሰባት ወራት ያለአሰልጣኝ የቆዩት ዋልያዎቹ የአሰልጣኝ ቅጥር ሊፈፀምላቸው ነው።

የኢትዮጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲሱ አመራር ከተመረጠ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት የመጪውን የውድድር ዘመን እና አጠቃላይ የስፖርቱን እንቅስቃሴ ብሩህ ለማድረግ በማሰብ ባደረገው ስብሰባ ፕሬዘዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጂራ መዋቅራዊ ለውጦችን የሚመለከት ምክረ ሀሳብ አቅርበው ነበር። በወቅቱ አጠቃላይ ያሉትን ችግሮች የሚያጠና ቡድን እንደተቋቋመም የሚታወስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንዲቀጠር አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን ይህን ሀላፊነት የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለነበሩት ለአቶ ሰውነት ቢሻው እንዲሁም ለአቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ፌዴሬሽኑ ዛሬ ከሰዐት በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ለመቅጠር በፅህፈት ቤቱ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል። በቀጣዮቹ አስር ቀናትም መስፈርቱን የሚያሟሉ አሰልጣኞች ማመልከቻዎቻቸውን እንደሚያስገቡ እና የመጨረሻውን ሰው ለመምረጥ የሚደረገው ምዘና እንደሚጀመር ይጠበቃል።

የቅጥር ማስታወቂያው ይህን ይመስላል።