አርባምንጭ ከተማ በደደቢት ላይ የተጫዋች ተገቢነት ክስ መስርቷል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ በደደቢት 2-1 የተረታው አርባምንጭ ከተማ የተገቢነት ክስ አቅርቧል፡፡

በአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ህልፈት ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው የ25ኛ ሳምንት የደደቢት እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ሰኞ እለት ተካሂዶ ደደቢት 2-1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በጨዋታው የደደቢቶቹ ሥዩም ተስፋዬ እና አቤል ያለው በ5 ቢጫ ካርድ ማረፍ ሲገባቸው ተሳትፈዋል በሚል አርባምንጭ ከተማ ዛሬ ለፌድሬሽኑ ደብዳቤ ማስገባቱን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ታዲዮስ ጨመሠ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልዋል፡፡ በዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔን እንደሚሰጥ ታውቋል።

ደብዳቤው ይህን ይመስላል