የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በ5 ሀገራት መካከል ይከናወናል

በተደጋጋሚ ሲራዘም የቆየው የ2018 የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በመጨረሻም በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 12 እስከ 19 እንደሚካሄድ ሲረጋገጥ በሊግ ፎርማት እንሚካሄድ ሴካፋ አሳውቋል።

ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በ2016 በዩጋንዳ አስተናጋጅነት 7 ሀገራት መካከል ተደርጎ በነበረው በዚህ ውድድር ላይ ዘንድሮ ኢትዮጵያ፣ አዘጋጇ ሩዋንዳ፣ የ2016 ቻምፒዮኗ ታንዛንያ፣ የፍጻሜ ተፋላሚዋ ኬንያ እና ያለፈው ውድድር አዘጋጅ ዩጋንዳ ብቻ እንደሚካፈሉ ያሳወቁ ሀገራት ሲሆኑ የተሳታፊዎቹ ቁጥር ማነስ ውድድሩን ከጥሎ ማለፍ ይልቅ በዙር መልክ እንዲደረግ አስገድዷል። እያንዳንዱ ቡድን አምስት ጨዋታ ካደረገ በኋላ የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበው ቡድንም የውድድሩ ቻምፒዮን ይሆናል።

ሐምሌ 12 በሚጀምረው ውድድር ኢትዮጵያ አራፊ ስትሆን ኬንያ ከዩጋንዳ እና ሩዋንዳ ከ ታንዛንያ የመጀመርያ ጨዋታዎች ናቸው።

                      ሙሉ መርሐ ግብር

ሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2010

09:00 ኬንያ ከ ዩጋንዳ

11:15 ሩዋንዳ ከ ታንዛንደያ

ቅዳሜ ሐምሌ 14 ቀን 2010

09:00 ኢትዮጵያ ከ ዩጋንዳ

11:15 ኬንያ ከ ታንዛንያ

ሰኞ ሐምሌ 16 ቀን 2010

09:00 ዩጋንዳ ከ ታንዛንያ

11:15 ሩዋንዳ ከ ኢትዮጵያ

ረቡዕ ሐምሌ 18 ቀን 2010

09:00 ኬንያ ከ ኢትዮጵያ

11:15 ዩጋንዳ ከ ሩዋንዳ

አርብ ሐምሌ 20 ቀን 2010

09:00 ኢትዮጵያ ከ ታንዛንያ

11:15 ሩዋንዳ ከ ኬንያ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2016 ውድድር በመሰረት ማኒ አሰልጣኝነት እየተመራ በ3ኛነት ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በአሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ የሚመራው የወቅቱ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው ወር በአልጄርያ ተሸንፎ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ መሆኑ ይታወሳል።