ለሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ዝግጅት 22 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

ከሀምሌ 12 እስከ 19 በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ ዝግጅት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ 22 ተጫዋቾችን ጠርታለች። የተጠሩት አመዛኝ ተጫዋቾች በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ላይ ያገለገሉ ሲሆኑ ወሳኛ አጥቂ ሎዛ አበራ ለሙከራ ወደ ስዊድን በማምራቷ እንዲሁም ሌላኛዋ አጥቂ ረሒማ ዘርጋ ከዝርዝሩ ተዘለዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በነገው እለት የሚጠናቀቅ ሲሆን ከዕሁድ ጀምሮ ተጫዋቾች ተሰባስበው አዲስ አበባ ለልምምድ ምቹ ባለመሆኑ ምክንያት አዳማ፣ ቢሾፍቱ አልያም ሀዋሳ በአንዱ ከተማ ዝግጅታቸውን እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ገነት አክሊሉ (ደደቢት)፣ ታሪኳ በርገና (ጥረት ኮርፖሬት )፣ ንግስት መዐዛ (ኢ/ንግድ ባንክ)

ተከላካዮች

መሰሉ አበራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ጊዮርጊስ)፣ ቤተልሄም ከፍያለው ( ኤሌክትሪክ)፣ አሳቤ ሙሶ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ መስከረም ካንኮ ( ደደቢት)፣ ታሪኮ ደቢሶ (ንግድ ባንክ)

አማካዮች

ቤዛዊት ተስፋዬ (ቅዱስ  ጊዮርጊስ)፣ አለምነሽ ገረመው (ኤሌክትሪክ)፣ አረጋሽ ካልሳ (ኢትዮ/ወጣቶች አካዳሚ)፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ)፣ ሰናይት ቦጋለ (ደደቢት)፣ ብርቱካን  ገ/ክርስቶስ (ደደቢት)፣ ትዕግስት ዘውዴ (ደደቢት)፣ ዙለይካ ጁሀድ ( ንግድ ባንክ)፣ ህይወት ደንጊሶ (ንግድ ባንክ)

አጥቂዎች

ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ)፣ ምስር ኢብራሂም (ጥረት ኮርፖርት)፣ ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ልደት ቶሎአ (ሀዋሳ ከተማ)

በ5 ሀገራት መካከል በሚደረገው የዘንድሮው ሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያ ሐምሌ 14 ላይ ከዩጋንዳ ጋር ትጫወታለች።