በርከት ያሉ የውጭ ተጫዋቾች በመጨረሻው የሊግ ጨዋታ ክለባቸውን አያገለግሉም

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ኮንትራታቸውን ያጠናቀቁ የውጪ ተጫዋቾች ክለቦቻቸውን አያገለግሉም፡፡ 

ይህን ፅሁፍ እስካጠናቀርንበት ሰዓት አምስት ክለቦች የውጭ ተጫዋቾቻቸውን አገልግሎት የማያገኙ ይሆናል። ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወሳኙ የመስመር አጥቂው ፕሪንስ ሰርቨርንሆን ውሉ በመጠናቀቁ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከቡድኑ ጋር የማይገኝ ሲሆን አዳማ ከተማ አይቮሪያዊው አማካይ ኢስማኤል ሳንጋሬ የመኖሪያ ፍቃድ በመጠናቀቁ፣ ኢትዮጵያ ቡና የናይጄሪያዊው ሳሙኤል ሳኑሚ ኮንትራት በመጠናቀቁ፣ ሀዋሳ ከተማ ከካሜሮናዊው አጥቂ ያቡን ዊሊያም፣ አርባምንጭ ከተማ ከጋናዊው ተከላካይ አሌክስ አሙዙ፣ ድሬዳዋ ከተማ ከሳውሬል ኦልሪሽ እና ሚካኤል አኩፎ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ከአብዱልፋታ ሰዒዱ ጋር በተመሳሳይ  ያላቸውን ዉል በማጠናቀቃቸው በመጨረሻው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ላይ አይካፈሉም።

ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘሁ መረጃ በርካታ ከሀገር  ውጭ የመጡ ተጫዋቾች ኮንትራታቸውን ሰኔ 30 ቢያጠናቅቁም ለቀሪ ጊዜያት ተጨማሪ ክፍያን በመክፈል ለመጨረሻ ጨዋታ አቆይተዋቸዋል። 

ሰኔ 30 ላይ የኮንትራት ውላቸው የተጠናቀቀ ተጫዋቾች ውድድሮች እስኪጠናቀቁ ድረስ በክለባቸው ይቆያሉ።