የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ተጀምሯል

የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በዛሬው እለት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል። ኢትዮጵያም ቅዳሜ የመጀመርያ ጨዋታዋን ታከናውናለች።
በመክፈቻ ጨዋታው 09:00 ላይ በስታደ ኪጋሊ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የዩጋንዳ እና ኬንያ ጨዋታ በዩጋንዳ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ሊሊያን ሙቱዞ የዩጋንዳ ብቸኛ ጎል ባለቤት ናት። 11:30 ላይ አስተናጋጇ ሩዋንዳ  አሊስ ካሊምባ በ34ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ጎል የ2016 ቻምፒዮኗ ታንዛንያን 1-0 አሸንፋለች። ይህን ጨዋታ ሊዲያ ታፈሰ በመሐል ዳኝነት ስትመራ ወጋየሁ አበራ በረዳትነት ዳኝታለች።

በ5 ሀገራት መካከል በዙር መልክ እየተከናወነ የሚገኘው ውድድሩ አንድ ቀን እረፍት እያደረገ የሚከናወን ሲሆን በመጪው ቅዳሜ የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ትላንት ወደ ሩዋንዳ ያመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም በስፍራው ልምምድ እያደረገ ይገኛል።

ቅዳሜ ሐምሌ 14 ቀን 2010

09:00 ኢትዮጵያ ከ ሩዋንዳ

11:30 ኬኔያ ከ ታንዛንያ

መረጃዎች እና ፎቶዎች – JSports1, Ethio Woman Sport,