ወላይታ ድቻ የአሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀን ኮንትራት አራዝሟል

በውድድር ዘመኑ አጋማሽ የወላይታ ድቻ ዋናው ቡድንን የተረከቡት አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በወላይታ ድቻ ለመቆየት ተስማምተዋል፡፡

የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ስንብት ተከትሎ ከ17 አመት በታች ወደ ዋናው ቡድን በመሸጋገር በመጀመርያዎቹ ወራት በተለይም በአፍሪካ መድረክ መልካም ጉዞ ቢያደርጉም በሊጉ እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ ላለመውረድ መታገላቸው የአሰልጣኙ የመቆየት ዕድል አጠራጣሪ ቢያደርገውም ለተጨማሪ አንድ ዓመት በድቻ ለመቆየት መስማማታቸውን የክለቡ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ክለቡም ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንደተቃረበ እና የተወሰኑ ተጫዋቾች ደግሞ እንደሚቀነሱ ፕሬዝዳንቱ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡