የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ድልድል ወጥቷል 

ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ ስድስት ቡድኖች የሚለዩበትና በ16 ቡድኖች መካከል ከሐምሌ 16 ጀምሮ በአዳማ ከተማ የሚካሄደው የኢትዮዽያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ድልድል ዛሬ ወጥቷል።

የባ ኢንተርናሽናል ሆቴል የፌዴሬሽኑ ዋና ፀኃፊ አቶ ሰለሞን ገ/ሥላሴ እና የአንደኛ ሊግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በተከናወነው ስነ-ስርዓት አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በመክፈቻ ንግግራቸው ለውድድሩ ስድስት ኮሚሽነሮች እና 16 ዳኞች የተመደቡ ሲሆን ውድድሩ የሚመራበት ደንብ የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብ ፣ የዲሲፕሊን ደንብ እና የአንደኛ ሊግ የውድድር ደንብ መሆኑ ገልጸዋል። በጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ የሚፈጠሩ ቅሬታዎች እዚሁ በተገኙ የውድድር አመራሮች ውሳኔ እንደሚያገኝና ውሳኔው ይግባኝ እንደሌለው አስረድተው ጨዋታዎቹም በአዳማ አበበ ቢቂላ እና በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ሜዳዎች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል።

ከየምድባቸው አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ ቡድኖች በቀጥታ ስምንት ውስጥ ይገቡና ከስምንቱ ቡድኖች ለግማሽ ፍፃሜ በሚያደርጉት ጨዋታ አሸናፊዎቹ አራት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡ ሲሆን ተሸናፊ ቡድኖች በወጣላቸው ዕጣ መሰረት በሚያደርጉት ጨዋታ አሸናፊዎቹ አምስተኛ እና ስድስተኛ ቡድን በመሆን ከፍተኛ ሊጉን የሚቀላቀሉ ይሆናል ።

በውድድሩ ላይ ክለቦች ጊዜያዊ ውጤት ፍለጋ ተገቢ ያልሆኑ ተጫዋቾች ይዘው እንዳይመጡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ በመስጠት በቀጥታ ወደ ምድብ ድልድሉ አምርተዋል።

የምድብ ድልድል

ምድብ ሀ ፡ ወላይታ ሶዶ፣ ዳሞት ከተማ፣ ሞጆ ከተማ፣ አሶሳ ከተማ

ምድብ ለ: ጎጃም ደብረማርቆስ፣ ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ፣ አራዳ ክ/ከተማ፣ ሺንሺቾ ከተማ

ምድብ ሐ: ቱሉ ቦሎ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ አርሲ ነገሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ

ምድብ መ፡ ራያ አዘቦ፣ ናኖ ሁርቡ፣ ገላን ከተማ፣ ትግራይ ውሀ ስራ

ሰኞ ሐምሌ 16 ቀን 2010

ምድብ ሀ

08:00 ወላይታ ሶዶ ከ አሶሳ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

10:00 ዳሞት ከተማ ከ ሞጆ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

ምድብ ለ

08:00 ጎጃም ደብረማርቆስ ከ ሺንሺቾ ከተማ (ዩኒቨርሲቲ)

10:00 ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ ከ አራዳ ክ/ከተማ (ዩኒቨርሲቲ)