ስምዖን ዓባይ በድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝነት አይቀጥሉም

ድሬዳዋ ከተማ ከስምንተኛው ሳምንት ጀምሮ ክለቡን በአሰልጣኝነት ሲመሩ የነበሩት አሰልጣኝ ስምዖን ዓባይን ከክለቡ አሰልጣኝነት አንስቷል።
የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ከክለቡ መነሳት ተከትሎ ከምክትል አሰልጣኝነት ወደ ዋናነት የተሸጋገሩት አሰልጣኝ ስምዖን ቡድኑን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ መርተው በመጨረሻው ጨዋታ ከመውረድ መትረፉ የሚታወስ ነው። ሆኖም በቀጣዩ የውድድር ዓመት በኃላፊነታቸው እንደማይቆዩ ተነግሯል። በነገው እለት የክለቡ ቦርድ በሚያደርገው ስብሰባም በቀጣዩ አሰልጣኝ ጉዳይ ላይ የሚመክር ሲሆን የስምዖን በምክትልነት የመቆየት እና የመቀጠል ጉዳይም ይታወቃል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና በቀጣዩ ቅዳሜ በክለቡ ዙሪያ ከከተማዋ ህዝብ ጋር ለመምከር መዘጋጀቱንም ሰምተናል፡፡