ሴካፋ 2018| ሉሲዎቹ የመጀመርያ ድላቸውን አሳክተዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የመጀመርያ ድሉን አስተናጋጇ ሩዋንዳ ላይ አስመዝግቧል።

ከትላንት በስቲያ በመጀመርያ ጨዋታው በዩጋንዳ 2-1 የተሸነፈው ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሩዋንዳን 3-0 በማሸነፍ ከመሪዎቹ ያለውን ልዩነት ማጥበብ ችሏል። በ32ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተመለሰውን ኳስ ወደ ግብነት ቀይራ የመጀመርያው አጋማሽ በሉሲዎቹ 1- መሪነት ሲጠናቀቅ በ66ኛው ደቂቃ ዓለምነሽ ገረመው ያሻገረችውን ኳስ ተጠቅማ ምርቃት ፈለቀ ሁለተኛውን አክላለች። በ75ኛው ደቂቃ ደግሞ ሴናፍ ዋቁማ ሶስተኛውን አስቆጥራ ጨዋታው በኢትዮጵያ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። 

ዛሬ በተካሄደ ሌላ ጨዋታ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ አሸንፋ የነበረው ዩጋንዳ በታንዛንያ 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፋለች። ታንዛንያ ማሸነፏን ተከትሎም የዋንጫው ፉክክር ላይ ነፍስ ዘርታበታለች። 

የደረጃ ሰንጠረዥ 

1. ዩጋንዳ 3 (-1) 6

2. ታንዛንያ 3 (+2) 4

3. ኢትዮጵያ 2 (+2) 3

4. ሩዋንዳ 2 (-2) 3

5. ኬንያ 3 (-1) 1

ቀጣይ ጨዋታዎች

ረቡዕ ሐምሌ 18 ቀን 2010

09:00 ኬንያ ከ ኢትዮጵያ

11:15 ዩጋንዳ ከ ሩዋንዳ

አርብ ሐምሌ 20 ቀን 2010

09:00 ኢትዮጵያ ከ ታንዛንያ

11:15 ሩዋንዳ ከ ኬንያ