አወል ዓብደላ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል

አወል ዓብደላ የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ በመሆን ወላይታ ድቻን ተቀላቅሏል። ተከላካዩ ወደ ክለቡ ከዓመታት በኋላ ተመልሷል።

የመሀል ተከላካዩ በሙገር ሲሚንቶ፣ ሀላባ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ቆይታ አድርጎ በ2005 ወደ መከላከያ ያመራ ሲሆን ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ በድጋሚ በ2009 ወደ ጦሩ ቤት ተመልሷል። አሁን ደግሞ ወደ ቀድኖ ክለቡ ወላይታ ድቻ የሚመልሰውን ፊርማ በዛሬው እለት አጠናቋል።

ወላይታ ድቻ ከአወል በተጨማሪ በጅማ አባ ጅፋር ድንቅ ዓመት ያሳለፈው አሚኑ ነስሩን ለማዛወር ከስምምነት ደርሷል። ዛሬ ወይም ነገ በፌዴሬሽን ተገኝቶ በይፋ ውል እንደሚፈራረምም ይጠበቃል።

ወላይታ ድቻ አስቀድሞ ታሪክ ጌትነት፣ ፀጋዬ አበራ፣ ኄኖክ ኢሳይያስ እና ሳምሶን ቆልቻን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው።