መከላከያ ተመስገን ገብረኪዳንን አስፈረመ

የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ወደ ተለያዩ ክለቦች መዘዋወራቸውን ቀጥለዋል። ተመስገን ገብረኪዳንም ወደ መከላከያ አምርቷል።

የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ በጅማ አባ ጅፋር ያለፉት ሁለት ዓመታት ስኬት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት የከፍተኛ ሊግ እና ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን በተከታታይ ማሳካት ችሏል። የጅማ ውል መጠናቀቁን ተከትሎም መከላከያን በ2 ዓመት ውል መቀላቀል ችሏል።

በ2005 በሰበታ ከተማ የክለብ እግርኳሰን የጀመረው ተመስገን ከሁለት ዓመት በኋላ በ2007 ወደ ፋሲል አምርቶ ከግማሽ የውድድር ዘመን በኋላ ከክለቡ ተለያይቶ ለ6 ወራት ያለ ክለብ ከተቀመገ በኋላ በ2008 ጅማ አባ ጅፋርን ተቀላቅሎ ለ3 ዓመታት ቆይቷል።

ባለፈው ክረምት ሁለት ተጫዋቾችን ብቻ አስፈርሞ የነበረው የሥዩም ከበደ መከላከያ ከወዲሁ ተመስገንን ጨምሮ አራት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።