ሥዩም ተስፋዬ ወደ መቐለ ከተማ አምርቷል

መቐለ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በስፋት ተሳትፎ ማድረጉን ቀጥሏል። አንጋፋው ሥዩም ተስፋዬንም ወደ ክለቡ መቀላቀሉ ተረጋግጧል። 

የቀድሞው የመተሐራ ስኳር እና ኒያላ ተጫዋች ሥዩም ተስፋዬ በ2003 ኤሌክትሪክን ለቆ ወደ ደደቢት ካመራ በኋላ የእግርኳስ ህይወቱ ከፍታ ላይ መድረስ ችሎ የነበረ ሲሆን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈው ብሔራዊ ቡድን አካል ከመሆኑ በተጨማሪ ከ2007 ወዲህ ለበርካታ ጊዜያት የዋልያዎቹ አምበል በመሆን አገልግሏል። የቀኝ መስመር ተከላካዩ የሊግ ቻምፒዮን በሆነበት ደደቢት 8 የውድድር ዓመታት ቆይቶ በመጨረሻም ከክለቡ ጋር በመለያየት ወደ መቐለ አምርቷል።

መቐለ ከተማ ዮናስ ገረመው፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ያሬድ ሀሰን፣ ጋብሬል አህመድ እና ሳሙኤል ሳሊሶን ሲያስፈርም ገብረመድህን ኃይሌን አሰልጣኝ ማድረጉ ይታወሳል።