ወልዋሎ ዳንኤል አድሓኖምን አስፈረመ

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዳንኤል አድሓኖምን አስፈርሟል። 

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ወደ መቐለ ከተማ አምርቶ ከአቼምፖንግ አሞስ ጋር በመፎካከር ጥቂት ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ሌላው የትግራይ ክለብ ማምራቱ ታውቋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ እስኪፈርስ ድረስ ቆይታ ያደረገው ዳንኤል በባንክ ካሰለጠኑት ጸጋዬ ኪዳነማርያም ጋር በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል።

ዳንኤል ከብርሀኑ ቦጋለ እና ቢንያም ሲራጅ ቀጥሎ 3ኛው የወልዋሎ አዲስ ተጫዋች አድርጎታል።