ጸጋዬ ኪዳነማርያም ውላቸውን አድሰዋል

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን በውድድር ዘመኑ አጋማሽ የተረከቡት አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማርያም በወልዋሎ ውላቸውን አራዝመዋል።

ዓመቱን አርባምንጭ ከተማን በማሰልጠን የጀመሩት አሰልጣኝ ጸጋዬ ከ8 ውጤታማ ያልሆኑ ጨዋታዎች ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር ተለያይተው የሁለተኛው ዙር መጀመርያ ላይ ወደ ወልዋሎ በማምራት ክለቡ ላለመውረድ ያደረገውን ትግል በስኬት እንዲያጠናቅቅ ረድተውታል። አሁን ደግሞ እስከ ቀጣዩ የውድድር ዘመን መጨረሻ ቢጫ ለባሾቹን ይዘው ለመቀጠል ውላቸውን ማደስ ችለዋል።

ወልዋሎ የቀድሞው የትራንስ ኢትዮጵያ፣ ሐረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ አሰልጣኝን ውል ከማደሱ በተጨማሪ ቢንያም ሲራጅ፣ አማኑኤል ጎበና፣ ዳንኤል አድሓኖም እና ብርሀኑ ቦጋለን አስፈርሟል።