አሚኑ ነስሩ ወደ መቐለ ከተማ አምርቷል

መቐለ ከተማ ከጅማ ጋር የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን የሆነው አሚኑ ነስሩን አስፈርሟል። 

በአማካይ ስፍራ የሚጫወተው አሚኑ በዓመቱ መጀመርያ ሀዲያ ሆሳዕናን ለቆ ወደ ጅማ አባ ጅፋር ካመራ በኋላ በውድድር ዘመኑ ወጥ አቋም በማሳየት ያጠናቀቀ ሲሆን ከወላይታ ድቻ ጋር መስማማቱ ቢነገርም ኮንትራት ባለመፈራረሙ በዛሬው እለት ወደ መቐለ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቋል። በጅማ የቡድን አጋሩ ከነበረው ዮናስ ገረመው እና አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ጋርም በመቐለ የሚገናኝ ይሆናል።

መቐለ ከተማ እስካሁን አሚኑን ጨምሮ 7 ተጫዋቾች አስፈርሟል።