አህመድ ረሺድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል

ውድድር ዓመቱን በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው አህመድ ረሺድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ተመልሷል። 

በ2007 ደደቢት ተስፋ ቡድንን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና በማምራት በፍጥነት የመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ መካተት የቻለው አህመድ ረሺድ “ሽሪላ” ከቡድኑ ጋር ተለያይቶ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቶ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በምስራቁ ክለብ አሳልፏል። አሁን ደግሞ ወደ ቡና በድጋሚ ወደ ቡና ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል። 

በውድድር ዓመቱ በርከታ ተጫዋቾችን በመስመር ተከላካይ ስፍራ ላይ ሲያሰልፉ የነበሩት ዲዲዬ ጎሜስ በሁለቱም መስመሮች መጫወት የሚችለው አህመድን ማግኘታቸው አማራጭ የሚያሰፋላቸው ይሆናል።